Tuesday, February 18, 2014

የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘጋቢ አደጋ እንደደረሰበት ተዘገበ

ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በመኪና እንደገጩትና “ገና እንገድልሃለን” የሚል ዛቻ እንደሰነዘሩበት ለፍኖተ ነፃነት መናገሩን ጋዜጣው ዘግቧል።

“ጋዜጠኛው ከአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር በፓርቲው ጽ/ቤት ቃለምልልስ አድርጎ ወደ መገናኛ አካባቢ ሲደርስ ኮድ 1 የታርጋ ቁጥር18345 የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ሆነ ብሎ አደጋ አድርሶበታል፡፡” ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።
“ገጭታቸሁኝ ወዴት ትሄዳለትሁ” በማለት ሲጠይቃቸውም “ገና እንገድልሃለን” ብለውት እንደሄዱ የገለጸው ጋዜጣው፣ በታክሲው ውስጥ ሹፌሩና አንድ ግለሰብ ብቻ እንደነበሩም ታውቋል፡፡
ስቱዲዮ እስከገባንበት ሰአት ድረስ የጀርመን ሬዲዮ በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።
Source: Ethsat

No comments:

Post a Comment