ድርቅ በምሥራቅ ኢትዮጵያ
የድርጅቱ አጥኚዎች እንዳስታወቁት በድርቁ ሰበብ ገበሬዎችም አርብቶ አደሮችም ከብቶቻቸዉን እየሸጡ፥ ዉሐና ሳር ፍለጋ ከመኖሪያ ቀያቸዉ እየተሰደዱ ነዉ።በስደቱ ምክንያት አንዳድ አካባቢ ግጭት መከሰቱንም አጥኚዎቹ አስታዉቀዋል
ለምግብ እጥረት ለተጋለጠዉ ለምሥራቅ ኢትዮጵያ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገዉ የዩናይትድ ስቴትስ የርዳታ ድርጅት አስታወቀ።USAID በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ የርዳታ ድርጅት ባለሙያዎች እንዳስታወቁት የመሕርም፥የበልግም ዝናብ በመሳቱ የምግብ ምርት ከአማካዩ ከሃያ-እስከ አርባ በመቶ የሚሆን ቀንሷል።የድርጅቱ አጥኚዎች እንዳስታወቁት በድርቁ ሰበብ ገበሬዎችም አርብቶ አደሮችም ከብቶቻቸዉን እየሸጡ፥ ዉሐና ሳር ፍለጋ ከመኖሪያ ቀያቸዉ እየተሰደዱ ነዉ።በስደቱ ምክንያት አንዳድ አካባቢ ግጭት መከሰቱንም አጥኚዎቹ አስታዉቀዋል።የዋሽግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል። http://www.dw.de/
No comments:
Post a Comment