We come to conclusion of ruling about 21 years this barbaric regime and to give up suffering of our people. Now, top leaders of this minority ethnic groups the so called Wayne, The Oromo People Democratic Organization (OPDO) and others Wayne mafia arrested and given to INTERNATIONAL COURT OF JUSTICE (I.C.J.) for war crimes, genocide and crime against humanity.
የተባበሩት አሸባሪዎች ለፍርድ ይቅረቡ
ወያኔ መራሹ የወንጀለኞች ቡድን በኢትዮጱያ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት በደል ከእለት ወደ እለተ እየከፋ መጥቷል፡፡ከብዙ ጥቂቱን መጥቀስ ቢያስፈልግ፡- ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ህልዉናዋ ተጠብቆ እንዳትቀጥል በኢንቨስትመንት ስም ገበሬዉን እና በአከባቢ ለረጅም ዘመን የሚኖሩ ንዋሪዎችን ሀላፊነት በጎደለዉ መንገድ ከአካባቢዉ በማፈናቀል ለባእዳን ኢንቨስተር በ99 አመት ኮንትራት አሳልፈዉ እየሸጡዋት ነዉ፡፡ ወያኔዎች ስልጣን ላይ ለዘመናት ለመቀመጥ በመፈለግ ብቻ ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ ሀገር ሆና እንድትቀጥል ግድ ሳይላቸዉ በከፋፍለህ ግዛ እስትራቴጂ፣ በብሄር ፖለቲካ መርዝ የህዝብ አንድነቱን አፈራርሰዉ የጎሪጥ እንዲተያይ፣ ህብረት እንዳይኖረዉ፣ ወንድም በወንድሙ ለይ መልካም አመለካከት እንዳይኖረዉ፣ አንድ ለአምስት በሚል የፖለቲካ እስትራቴጂ አንዱ አንዱን እነዲሰልል እና መብቱን እንዳይጠይቅ አድርገዉታል፡፡
የአንድ ሀገር የበላይ ህግ ሆኖ የሚያገለግለዉ ህገመንግስት (Constitution ) ቢሆንም ኢትዮጵያ ዉስጥ እየታየ ያለዉ የተገላቢጦሽ ነዉ፤ ማለትም የተለያዩ አዋጆችን (Proclamations)እና ደንቦችን (Regulations) በማዉጣት ያወጡትን ህገመንግስት ያፈርሱታል፡፡ ለምሳሌ ብጠቅስ በወያኔ ህገመንግስት አነቀፅ 29 ላይ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብትን ይደነግጋል፤ ይህ አንቀፅ በምንም መንገድ ሊፈርስ አይችልም የልቁንም ሊሆን የሚግባዉ የሚወጡ አዋጆችና ደነቦች ህገመንግስቱ በሚፈቅደዉ መሰረት ሊተረጎሙና ሊተገበሩ በተገባ፡፡ በተግባር ይህ እንቀፅ ስራ ላይ ዉሏል ለሚለዉ ፍርዱን ለአንባቢ እተዋለሁ ምክንያቱም አሁን እያየን ያለነዉን የመናገር የመፃፍ ነፃነት ማጣትን በጋዜጠኞቻችን በእነ እስክንድር፤ እርዮት፤ አለምሰገድ እና ሌሎችም ችግሩ በስፋትና በጥልቀት እንዳለ ማሰረጃ መቁጠር አይጠበቅም፡፡
ወያኔዋች እራሳቸው ያወጡትን ህገመንግስት መልሰው እራሳቸዉ ሲጥሱት ይታያሉ፡፡ እራሳቸዉ ያላከበሩትን ህገመንግስት ሌሎች እንዲያከብሩት ያስገድዳሉ፤ ባለቤቱ ያላከበረዉን አሞሌ ጨዉ ... እንደሚባለዉ አባባል ማለት ነዉ፡፡ እነሱ ሲጥሱት ትክክል ናቸዉ ሌሎች ሲተላለፉት አሸባሪዎች ናቸዉ፡፡ የፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 እና የበጎ አድራጎትና መሀበራት ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጡ አዋጆችን ብንመለከት አዋጅ ቁጥር 12/2001 በአብዛኛዉ ህገመንግስቱን የሚጣረሱ ናቸዉ፡፡ ዝርዝር ትንታኔዎቹን ወደፊት እመለስበታለሁ፡፡
ለዘመናት ተከባብሮና ተፋቅሮ የኖረን ህዝብ የሀይማኖት አክራሪነትን በማስፋፋት ሀገር ሰላም እንድታጣ እያደረጟት ይገኛሉ፤ ሴት እህቶቻችንን ለሴተኛ አዳሪነት እና ለአረብ ሃገራት ግርድና ሰለባ ዳርገዋቸዋል፡፡ ህፃናት ልጆችን በቸልተኝነት ለምእራብያዉያን ሀገራት በማደጎ በመስጠት፡ ኢትዮጵያዊ ወጋችን በማይፈቅደዉ ልማድ ልጆች ለግብረ ሰዶም እና ሰብአዊነት በማይሰማቸዉ አሳዳጊዎች የዉስጥ ብልቶቻቸዉን ለገበያ በማቅረብ ሲጫወቱባቸዉ ግድም አይላቸዉም፡፡
እነዚህን እና ሌሎች ያልጠቀስኯዋቸዉን ወንጀሎች ከላይ በፎቶዉ ላይ የምትመለከቱዋቸዉ መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ ቢሞትም ኢትዮጵያን የማጥፋት ተግባራቸዉን አላቆሙም፡፡ እናም ሀገር የማጥፋት ስራቸዉን አቁመዉ አለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸዉ እላለሁ፤ እርሶ ምን ይላሉ በሀሳቤ ከተስማሙ ላይክ እንዲያደርጉ በኩሩዉ ኢትዮጵያዊዉ ስም እጠይቅዎታለሁ፡፡ አመሰግናለሁ
ኢትዮጲያችን ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር! አሜን
አሚን
ReplyDelete