በአፋር ክልል ነዋሪዎችን የማፈናቀሉ ዘመቻ ቀጥሎታል
የካቲት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከክልሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሸንኮራ አገዳ ልማት ጋር በተያያዘ ተጠናክሮ የቀጠለው የህዝብ መፈናቀል ህብረተሰቡን ለከፋ ድህነት እየዳረገው ነው። የመንግስትን ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ ሴቶች እስከ ልጆቻቸው መታሰራቸውን የክልሉ የመኢአድ ጠጠሪ የሆኑት አቶ አሊ ሚራህ ለኢሳት ገልጸዋል ህዝቡ ጉዳዩን ገለልተኛ አካል መጥቶ እስከሚያየው ድረስ ከቦታችን አንነሳም ማለቱን አቶ አንፍሬ ተናግረዋል::
በአፋር፣ በቦረና ዞን እና በዋልድባ አካካቢዎች ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ የሚታየውን የህዝብ መፈናቀል ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment