Tuesday, March 12, 2013

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የዕድገትና የለውጥ ዕቅድ ግምገማ


ኢትዮጵያ

የዕድገትና የለውጥ ዕቅድ ግምገማ

በኢትዮጵያ የዕድገትና ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) ዕቅድ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ግማሽ ጊዜው የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የአፈፃፀም ሂደቱን የተመለከተ ግምገማ ባለፈው ሳምንት ቀርቦ ነበር። መንግስት የኢትዮጵያ የእድገትና የለውጥ ዕቅድ አፈፃፀም ውጤታማ ነው ሲል አስታውቀዋል። በዋና ዋና ዘርፎች ግን ከዕቅድ በታች የሆነ ውጤት መዝገቡም በስብሰባው ገልጿል።
በኢትዮጵያ የዕድገትና ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) ዕቅድ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ግማሽ ጊዜው የተጠናቀቀ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪቃ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፈፃፀም ሂደቱን የተመለከተ ግምገማ ቀርቦ ነበር። በግምገማው የኢትዮጵያ የእድገትና የለውጥ ዕቅድ አፈፃፀም ውጤታማ ነው ሲል መንግስት አስታውቋል። በዋና ዋና ዘርፎች ግን ከዕቅድ በታች የሆነ ውጤት መዝገቡም በስብሰባው ላይ ተገልጿል። በጀርመን የአፍሪቃ የሠላምና የኢኮኖሚ እድገት አማካሪ ድርጅት ሃላፊና የኢኮኖሚክስ ምሁሩ ዶክተር ፈቃደ በቀለ የመንግስት ዘገባ የተብራራ እንዳልሆነ በመጥቀስ ዕቅዱ ሊያካትት ይገባቸው የነበሩ አበይት ጉዳዮች እንደሚጎድሉ ይናገራሉ።
መንግስት ያቀደው የ11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት በሁለተኛው ዓመት አፈፃፀም መሰረት ወደ 8.5 በመቶ ዝቅ ማለቱን አስታውቋል። ዶክተር ፈቃደ ይህ የሚያሳየው ነገር አለ ይላሉ።
በተለይ ደግሞ በዓመት ከ3.1 በመቶ በላይ የሆነው የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር እድገት ከኢኮኖሚው እድገት ጋ አልተጣጣመም ሲሉ ዶክተር ፈቃደ አፅንኦት ይሰጣሉ።
በዚሁ ግምገማ ላይ እንደተገለፀው የግብርናው ዘርፍ አፈፃፀሙ ከሌሎቹ ጋ ሲነፃፀር ከዕቅድ እጅግ አነስ ብሎ ነው የተገኘው። ምክንያቱ ምን ይሆን? ዶክተር ፈቃደ በተለይ በእርሻው ኢኮኖሚ ላይ ታላቅ ተፅዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝረዋል። http://www.dw.de

No comments:

Post a Comment