Sunday, March 17, 2013

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ


ARCHIV - Pakistanische Journalisten protestieren in Karachi gegen die Behinderung ihrer Arbeit (Archivfoto/Illustration vom 16.03.2007). Die Vereinten Nationen begehen auf Initiative ihrer Kulturorganisation UNESCO seit 1994 jährlich am 3. Mai den Tag der Pressefreiheit. Foto: Nadeem Khawer (zu dpa-Themenpaket vom 28.04.) +++(c) dpa - Bildfunk+++
pixel

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ

የኢትዮጵያ መንግሥት በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ስሞታ ያቀርባሉ ።
አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች የውጭ መንግሥታት የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደማይከበሩ በተለያዩ ጊዜያት በሚያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እነዚህን ዘገባዎች አይቀበልም ። ይልቁንም በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች መብቶችን በሚጥሱ ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶችና የውጭ መንግሥታት እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስሞታ ያቀርባሉ ። እነዚህ ወቀሳዎች የሚቀርቡበት መንግሥት በቅርቡ «ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር » ያለውን ሠነድ አዘጋጅቷል ። በተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የዚህ የድርጊት መርሃ ግብር ፋይዳ ና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወይ የመነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው ። በነዚህ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩልን አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ አቶ እንዳልካቸው ሞላ በቀድሞው አጠራሩ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሃላፊ እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ተመራማሪን ጋብዘናል ። ሙሉውን ውይይቱን ያድምጡ ።http://www.dw.de/

No comments:

Post a Comment