Tuesday, December 31, 2013

የማዕድን ሥራዎች አዋጅ ፀደቀ

       01 JANUARY 2014 ተጻፈ በ  
 አዋጁ የመንግሥትን ነፃ ድርሻ ከፍ ያደርጋል

የማዕድን ሥራዎች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ፡፡ አዋጁ በማዕድን ዘርፍ በሚሰማሩ ድርጅቶች ላይ መንግሥት የሚኖረውን ድርሻ ከፍ ያደርጋል፡፡

በሥራ ላይ የሚገኘው አዋጅ መንግሥት በማዕድን አምራች ኩባንያዎች ላይ ያለምንም ክፍያ ከ0.1 በመቶ እስከ አምስት በመቶ የአክሲዮን ድርሻ እንዲኖረው ቢፈቅድም፣ ታኅሣሥ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ ግን የመንግሥት ድርሻ አምስት በመቶ እንዲሆንና ከዚህ ዝቅ እንዳይል ደንግጓል፡፡
የአነስተኛ ወይም የከፍተኛ ደረጃ የማዕድን ሥራ ፈቃድ አግኝቶ የተሰማራ ድርጅት ለንግድ በሆነ መጠን ማዕድን ማምረት ከጀመረበት ቀን አንስቶ ለመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ሊያሠሩት የሚችሉ ማናቸውንም አላቂ ዕቃዎች፣ ከቀረጥና ታክስ ነፃ ማስገባት እንደሚችል በፀደቀው አዋጅ ተካቷል፡፡

ማንኛውም ማዕድን አምራች ያመረተውን መጠን እያንዳንዱ ወር ባለቀ በአሥር ቀናት ውስጥ ፈቃድ ለሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚገባው፣ ላኪዎች ደግሞ ያመረቱትን ማዕድን ሩብ ዓመት በተፈጸመ ሰላሳ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መሸጥና ማሳወቅ እንደሚገባቸው ይደነግጋል፡፡ 

No comments:

Post a Comment