(ዘ-ሐበሻ) “ባለፉት ወራት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ሥነምግባራቶች በመከሰታቸውና ያለመግባባት በመፈጠሩ፤ ይህን ተከትሎ በማህበረ ምህመናኑ (አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶችና ህፃናት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ከነገ ታህሳስ 13 ቀን 2013 (December 21,2013) ጀምሮ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ለጊዜው እንድናቋርጥ ተገደናል” ይላል በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመንበረ ጸባዖት ቅድስ ሥላሴ ቤ/ክ ደጃፍ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ።

በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ያለው የስቶክሆልሙ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከገለልተኛነት ወደ ኢትዮጵያው ሲኖዶስ ለማስገባት ውሳኔ እንዲሰጥ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ይህን ተከትሎም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ቦርዱ በመግለጫው ላይ እንዳለው ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ሥነምግባራቶች መከሰትና ያለመግባባትም መፈጠር ጀምሯል።
የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቦርድ እና ሰበካ ጉባኤው ይህን አለመግባባት ለማብረድ ቤተክርስቲያኑን ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቱን ያሳወቀ ሲሆን “ወደፊት ያለውን ሂደት ለማህበረ ምዕምናን እና ምዕመናቱ እናሳውቃለን” ብሏል።
No comments:
Post a Comment