Wednesday, January 1, 2014

በኢትዮጵያ የተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እየከለከሉን ነው ሲሉ 18 የቻይና ኩባንያዎች አመለከቱ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል።                         ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው ጋዜጣው፣ በእነዚህ የመሠረተ ልማት ዘርፎች የተሰማሩት የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰኑ ባለሥልጣናት ቀደም ብለው ለገቡ የቻይና ኩባንያዎች ያለ ውድድር ሥራ እንደሚሰጡዋቸው፣ ደካማ የሥራ አፈጻጸም እያለባቸውም አንዱን ሥራ ሳይጨርሱ ተጨማሪ ሥራዎችን በላይ በላዩ ይሰጧቸዋል የሚል ቅሬታቸውን ዘርዝርው ለመንግስት አቅርበዋል።
ጥቂት ነባር የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ገንዘብ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን የመያዝ እንዲሁም ከቻይና መንግሥት በሚገኝ ብድር የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን የመቆጣጠር አዝማሚያ እያሳዩ መምጣታቸውን ጠቅሰዋል።                                   ነባር ኩባንያዎች ሥራዎችን የሚያገኙት ከተወሰኑ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር ነው የሚሉት አዲሶቹ ኩባንያዎች፣ ለሌሎች ኩባንያዎች ክፍት ሳይደረግ በቀላሉ በቢሊዮን የሚቆጠር ዋጋ ያለው ሥራ እንደሚሰጣቸውም ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት አንዳንድ ባለሥልጣናት በተጨማሪ ቻይና ኤምባሲ ውስጥ ቦታ ያላቸው ግለሰቦችም ለተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች እንደሚያዳሉ ያስረዳሉ ሲል ዘገባው ጠቅሷል፡፡ሌሎቹን በመግፋት የተወሰኑትን የሚተባበሩ በመሆኑ ብዙኃኑ የቻይና ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ማግኘት እንዳይችሉ መደረጉንም በመግለጽ መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ እንዲያጣ ከመደረጉም …click here to continue reading

No comments:

Post a Comment