በ8 ወር የስልጣን ቆይታው 14 ሴቶችን ስልጣኑን መከታ በመድረግ ፆታዊ ጥቃት ያደረሰው የማይጨው ሆስፒታል ዋና ስራ
ኣስኪያጅ( CEO) ከአምስት ቀናት በፊት( በባሇፇው እሮብ) በሀኪሞችና ሰራተኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ከስራው እንዲታገድ ተደርጓል፡፡
አቶ ብርሀኑ ይባላል እንደብዙዎቹ የክልለ የሆስፒታልች ስራ-አስኪያጅ በተፋጠነ የኤች .ኦ (Accelerated Health
Officer) በ1 ዓመት ከምናምን ትምህርት ጤና መኮንነት የተሰጠው ነው፡፡ ከዚህ በፉት “ዐዲሹሁ” በተባለ ጤና-ጣብያ ስራ- አስኪያጅ ሁኖ ሰርቷል፡፡
እዛ በሚሰራበት ጊዜም ብዙ ተመሳሳይ ሀሜቶች ይሰሙ ነበር፡፡ብዙ ሴት ሰራተኞች ላይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ ፆታዊ ጥቃት እንዳደረሰ ብዙ ሀሜቶች እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡ ሌሊ ቀርቶ ለኢ.ህ.አ.ዲ.ግ ድርጅታዊ ስልጠና ጦላይ በሄደበት ወቅትም አንዶን ሰልጣኝ ሴት ደፍሮ በእርቅ እንደለቀ ተሰምቷል፡
ይህ የአስገድዶ መድፈር ሱሰኛ የማይጨው ሆስፒታል ሐላፊ ሁኖ የተሸመው የዛሬ 8 ወር አካባቢ ነው፡፡
አቶ ብርሀኑ ሆስፒታሉን እግሩ ከረገጠበት ጊዜ አንስቶ የሆስፒታሉ ሰራተኞችን ሲሆንለት እያባበለ፣ አንዳንዴም ስልጣኑን በመመካት እያስፈራራ እስካሁን በውል የታወቁ 14 ሰራተኞችን ፆታዊ ጥቃት አድርጓል ተብሏል፡፡ ከዚሁ ውስጥ አንዷን ነርስ በጉልበት በቢሮው ቆልፎ እንደደፈራት ተሰምቷል፡፡
በፖለቲካዊ ታማኝነት መስፈርት የሚሾሙ ፍፁማዊ የሆነ ስልጣን የተሰጣቸው የሆስፒታል CEOዎች በተለይ በዚህ ክልል የጤና ሴክተሩን ያቀጨጨና ትልልቅ ባለሙያዎችንም ፈፅሞ ከሃላፊነት እንዲርቁና ባለው እንዲህ ዓይነቱ ምግባረ-ብልሹትና የአሰራር ግድፈቶች ሙያቸውን በተገቢ እንዳይተገብሩ ገድቧቸው እንዳለ ከብዙ ከፍተኛ ሐኪሞች በተደጋጋሚ የሚሰማ ነው፡፡ ይህ አሁን የምናወራበት ጉዳይም አንድ ማሳያ ሁኖ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡
እንደማንኛውም ሆስፒታል በሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሚመራ የስልጠና ኮሚቴ ነበር፡፡ ሰውየው ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ይሀንን ኮሚቴ አፍርሶ ስልጣኑን ለራሱ ይዞታል፡፡ ስልጠና በመጣ ቁጥር ማንንም ሳያማክርና ያለወረፋቸውን የፈለጋትን ሴት ሰራተኛ እየመረጠ ለስልጠናዎች እየላከ ለዋለላቸው ውለታም በገላቸውን እንዲመልሱለት ማስገደድ፣ ማባበል ዋና መለያ ባህርይው ሁኖና ብዙ የውስጥለውስጥ ሹክሹክታዎች እያስተናገደና ሆስፒታሉ እየታመሰ ቆይቷል፡፡
ይህ ስራ-አስኪያጅ የሆስፒታሉን መንፈስ አደፈረሰው፡፡ ከሰራተኛው ሁሉ መናጨት ጀመረ፡፡ የሀኪሞችም ስራ ማስተጓጎል ስራው አደረገው፡፡ የወረዳውና የዞኑ ሐላፊዎች እንዲሁም የሆስፒታሉ አመራር ቦርድ በሆስፒታሉ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ቢሰማም እርምጃ ለመውሰድ ግን ዳተኛ ነበር፡፡
ነገሮች በዚሁ እየቀጠሉ ባለበት ሁኔታ አሁንም እንደሁልጊዜው የ1 ወር ሞያዊ ስልጠኛ ዕድል ይመጣና አንድን የሆስፒታሉ ነርስን ማንንም ሳያሳውቅ ይልካታል፡፡ የ1 ወር ስልጠና ጨርሰች፡፡ ስልክ ደውሎም “ግድየለም ስልጠና ላይ ስትደክሚ ስለነበርሽ አንድ ሳምንት አርፈሽ ነይ: በኔ ይሁንብሽ” ይላታል፡፡
ተመልሳ ስራ የጀመረች ቀን እንደለመደው ያንን ውለታውን በገላዋ እነድትመልስ ይጠይቃታል፡፡ ይበልጥ የሚገርመው እቺ ሰራተኛ ባለትዳርና የልጆች እናት ናት፡፡ አልተስማማችም፡፡ “አለዚያ አንድ ሳምንት ያለፍቃድ አሳልፋ መጣች” ብየ እቀጣሻለሁ ብሎ ማስፈራራት፡፡ ወይ ፍንክች፡፡ በዚህ ሁኔታ ነገሩ ይፋ ተሰማ፡፡ አንድ ሁለት እያሉ በፍርሀት ጉዳቸውን አፍነው ዝም ያሉት ሌሎች ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችም እየተግተለተሉ በግልፅ መውጣት ጀመሩ፡፡ 14 ደረሱ፡፡
የሆስፒታሉ 6 ሓኪሞች፣ ጥቃቱ የደረሰባቸው ሴቶች አንድ ላይ ሁነው የሆስፒታሉን የበላይ አመራር ቦርድና የዞኑ አስተዳዳር እንዲያነጋግራቸው ጠሩ ይህ ጉዳይም ይፋ ወጣ፡፡
ታድያ የሚገርመው ቦርዱ፡ “ይህ ሰው ለረዥም ጊዜ ታማኝ የፓርቲው ነባር አባል እንደሆነ ነው መንግስት የሚያውቀው፡፡ እኛ አሁን እርምጃ ለመውሰድ ይከብደናል፡፡ ስለዚህ ነገሩ በደምብ እስቲጣራ በቦታው ይቆይ፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሐይሌ አስፍሀ ለስራ ወደ ውጪ ስለሄዲ ሲመለሱ እርምጃ ይወስዱበታል” ብሎ ምላሹን ሰጠ፡፡
ሓኪሞቹና ተበዳዮቹ ክፉኛ ተቆጡ፡፡ በዚሁ ሁኔታ ወደ ስራ እንደማይመለሱ በየቀኑ የሴት ልጅ በሚደፈርበት ሆስፒታል ሊሰሩ እንደማይችሉና ዛሬውኑ እንደሚለቁ አስረግጠው ተናገሩ፡፡ቦርዱም አማራጭ በማጣት ያለፈው እሮብ ቀን(ከ5 ቀን በፊት) ከስራው ታግዶ እነዲቆይ አድርጓል፡፡
የተበደሉትንም ሴት ሰራተኞችም “መጀመርያ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበትና ወደ ህጉ ደግሞ ቀጥላችሁ ትሄዳላችሁ” ተብለው እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡
እስካሁን የተመሰረተበት ክስ ግን የለም፡፡
No comments:
Post a Comment