ሳዲቅ አህመድ እንደዘገበው
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ ፖሊስ በሃሰተኛ ወንጀል አዲስ ክስ እንደመሰረተባቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ረቡዕ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በ 2004 በመኪና ሰው ገጭተው አምልጠዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ክሱን ለፍርድ ቤቱ በንባብ ያሰማ ሲሆን ሀምሌ 8 2004 ላይ በተለምዶ ሶማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ላይ በንብረት እና በሰው ሂወት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መልኩ ከተገቢው ፍጥነት በላይ አሽከርካሪውን በማሽከርከር በአንድ ሰው የእጁ አውራ ጣት ላይ የስብራት አደጋ አድርሰው ጥለውት ሄደዋል የሚል ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡
ይህም ድርጊት ተፈፀመ የተባለው ሃምሌ 8 ቀን የደህንንንት ሃይሎች የኮሚቴውን አመራሮች ከመንገድ ላይ በማገት ወደ ሚፈልጉት ቦታ የብልግና ስድብ እየሰደቡ ይዘዋቸው በሚወስዱበት ሰአት መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ቀን መታቂያቸውን አናሳይም ያሉት ደህንነቶች ጋጠወጥ በሆነ መልኩ ብልግና እየተሳደቡ ለማገት ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ አምልጠው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት ነው ሰው ገጭታችሁ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ወንጀል የቀረረበባቸው፡፡
ኡስታዝ አበቡበከር አህመድ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወንጀል መርማሪ ፖሊሶች ወደሳቸው በመሄድ ይህን ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከርም የተባለውን ድርጊት አለመፈፀማቸውን በወቅቱ መኪና ሲያሽከረክሩ እንዳልነበር፣መኪናውም የሌላ ሰው እንደነበር እና በሹፌር ሲሄዱ እንደነበር ብሎም ከፊት ለፊት በነበረው የመኪና መቀመጫ ላይም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተቀምጠው እንዳልነበር እና በደህንነቶች ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ የእገታ ወንጀል ሲፈፅምባቸው ከወንጀል ድርጊቱ ማምለጣቸውን በዝርዝር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህንንም በማስመለከት ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ሰአት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተው እንደሆነ ለማረጋገጥ የጠየቃቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድም ቃላቸውን መስጠታቸውን እና የዚህ አይነት ድርጊት በወቅቱ አለመፈፀሙን ብሎም የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የጠየቀ ቢሆንም አለመገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ምስክር የተባለ አንድ ግለሰብ ብቻ ግን ችሎት የቀረበ ሲሆን ሁሉም ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 28 ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይህ ክስ ሆን ተብሎ የኡስታዝ አቡበከር አህመድን ፅናት ለመፈታተን እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ተግባር ሲሆን በተጨማሪም ኮሚቴው በእስር ላይ ሆነው ባወጡት መግለጫ በመበሳጨታቸው እና የተፈጠረው መነቃቃት ወደሌላ አቅጣጫ ሆን ተብሎ ለማስቀየስ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ለትውስታ
ኢቲቪ በአቡበከር ላይ ሃሰተኛ ቪድዮ ሰርቶ ከለቀቀ በኋላ በስህተት ኤዲት ያልተደረገውን ቪድዮ ለቆት እንደነበር ይታወሳል፤ በድጋሚ ይመልከቱት
ኢቲቪ በአቡበከር ላይ ሃሰተኛ ቪድዮ ሰርቶ ከለቀቀ በኋላ በስህተት ኤዲት ያልተደረገውን ቪድዮ ለቆት እንደነበር ይታወሳል፤ በድጋሚ ይመልከቱት
No comments:
Post a Comment