Wednesday, January 15, 2014

ቻይና የጃፓኑ መሪ ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸው ተቃውሞዋን ገለጸች።

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበው የቻይና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉትን የጃፓኑን ጠ/ሚ ሽንዞ አቤን ችግር ፈጠሪ ብለዋቸዋል።
በአይቮሪኮስት፣ ሞዛምቢክና ኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ የመጡት ጠ/ሚ አቤ ለአፍሪካ አገራት ከፍተኛ የእርዳታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል በመግባት የቻይናን ተጽእኖ ለመቋቋም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።.በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደርና የአፍሪካ ህበረት ተወካዩ ሚ/ር ዚ ዚያዎን ፣ ጠ/ሚንስትሩ እስያ ውስጥ ችግር እየፈጠሩ ያሉ ሰው ናቸው ብለዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ ቻይናዎች ወደ ጃፓን ኢምባሲ በመሄድ ተቃውሞ ለማሰማትና ኢምባሲውን ፎቶ ግራፍ ለማንሳት በሄዱበት ወቅት ከጃፓን የጸጥታ ሰራተኞች ጋር መጋጨታቸውን ጋዜጣው አክሎ ዘግቧል።ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ አገር እየሆነች ነው። ኢትዮጵያ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከቻይና በብድር መልክ አግኝታለች። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶችም በቻይናውያን የተያዙ ናቸው።

1 comment:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    ReplyDelete