Friday, January 17, 2014
(የአፅቢ ወንበርታ ህዝባዊ ዓመፅ) ህዝብ ተበትኗል፣ መንግስት ካሳ ይከፍላል፣ የታሰሩ አይፈቱም
የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባፈለግ፣ ቁሸት ሕኖይቶ) ህዝብ የከፈተው ዓመፅ ዛሬ (ዓርብ 09/05/06 ዓም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ከአስር ደቂቃ (12:10) ላይ ቆሟል። ህዝብ ወደየቤቱ ተመልሷል። የፀጥታ ሃይሎች ግን ከአከባቢው አልራቁም።
አስተዳዳሪዎች ህዝቡን በፌደራል ፖሊስ አስከብበው ሲያስፈራሩት የዋሉ ሲሆን የህዝቡን ጥያቄ (ካሳ የመክፈሉ ጉዳይ) ለመመለስ ተስማምተዋል። ስለዚህ ህዝቡ በጠየቀው መሰረት መንግስት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል። የታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች ግን አይፈቱም። ህዝቡ "የታሰሩትን ይፈቱልን" ብሎ ሲጠይቅ "እርምጃ እንወስድባችኋለን፣ ማንም መጥቶ አያድናችሁም" የሚል ማስፈራርያ ደርሷቸዋል። ስለዚህ መንግስት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩትን ዜጎች ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለም።
የመንግስት አካላት ህዝቡን ካሳ ለመክፈል ሲስማሙ የህዝቡን ጥያቄ ትክክለኛነት ተቀብለውና አምነው እንደሆነ አቅርበዋል። ጥያቄው ያነሱት ዜጎች ከእስር ለመፍታት ግን ፍቃደኛ አይደሉም። በትግራይ ዜጎች መብታቸው ሲጠይቁ ለእስር ይዳረጋሉ። የአፅቢ ወንበርታ ጠያቂዎች ምሳሌ ናቸው። ታሳሪዎች የዛሬን ጨምሮ ስምንት ናቸው።
ጥያቄ የጠየቀ ዜጋ ለምን ይታሰራል? ጥያቄ የመጠየቅ መብት የለውም? መንግስት የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ለምን ወደ ሃይል እርምጃ ይሄዳል? አምባገነኖች በራስ የመተማመን ባህሪ ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።
Source:Abraha Desta
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment