ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 59 ገድለው፣ 42 አቁስለዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል።
“በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ሰላም ካገኙ ለተቃዋሚዎች ምቹ ቦታ ሊፈጥሩ ይችላል በሚል እሳቤ የሁለቱን ክልል ህዝቦች እያጋጨና እርስበርስ ተጠባብቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ” መንግስት ግጭቱን ሆን ብሎ መቀስቀሱን የገለጡት ዶ/ር ኢብራሂም ፣ በግጭቱም እድሜውን ለማራዘም እንደሚያስብ ተናግረዋል። ማህበሩ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ለሌሎችም አገራት ደብዳቤ ማስገባታቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል ።

No comments:
Post a Comment