Sunday, January 19, 2014

ሃኒከን ‹‹ኒያላ›› በሚል ስያሜ አዲስ ቢራ ለማምረት ቅድመ ዝግጅት ጀመረ


ከሁለት ዓመት በፊት የሐረርና የደሌ ቢራ ፋብሪካዎችን በመግዛት የኢትዮጵያ የቢራ ኢንዱስትሪን የተቀላቀለው ግዙፉ የሆላንድ ቢራ ጠማቂ ሃኒከን፣ ‹‹ኒያላ›› በሚል ስያሜ አዲስ የቢራ ምርት ለማምረት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
ኩባንያው አዲሱን ቢራ አምርቶ ወደ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችለውን ስያሜ በማስመዝገብ፣ በጠየቀው ስያሜ መሠረት ፈቃድ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ፋብሪካው በአዲስ አበባ ቂሊንጦ ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ግዙፍ የፋብሪካ ግንባታ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የቂሊንጦ ፋብሪካው በዓመት 1.5 ሚሊዮን ሔክቶ ሊትር ቢራ ለማምረት የሚያስችል አቅም እንዳለው የገለጸ ሲሆን፣ ለግንባታውም 120 ሚሊዮን ዩሮ መመደቡ አይዘነጋም፡፡
ሃኒከን ‹‹ኒያላ›› የሚለውን ስያሜ በሌላ ተመሳሳይ የንግድ ድርጅት ከተያዘ በዚህ ስያሜ የቢራ ምርት ማቅረብ አይቻልም፡፡ ሆኖም ‹‹ኒያላ›› የሚለውን ስያሜውን ሊቃወም የሚችል ተቋም እንዳለና እንደሌለ ለማረጋገጥ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡
በአገሪቱ ብርቅዬ እንስሳ በሆነው ‹‹ኒያላ›› ስያሜ ምርቱን ማምረት ከተቻለ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ሃኒከን በብቸኝነት የሚያቀርበው አዲስ ምርት ይሆናል፡፡  

No comments:

Post a Comment