በመረጃው መሰረት የኣዲስ ኣበባ ከተማ ነጋዴዎች በላያቸው ላይ እየደረሰ ባለው የስራ መስተጓጎል ተግባር ኣስመልክተው እንደገለፁት፤ የተወሰነባቸው የመንግስት ግብር በግዜው እንዳይከፍሉ የፅህፈት ቤቱ ሃላፊዎች የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ እያመላለስዋቸው እንዳሉ’ና በዚህ ምክንያትም ነጋዴዎቹ ግብር የሚከፉሉበት ቀን በማለፉ ምክንያት ላልተፈለገ ቅጣት እየተጋለጡ መሆናቸው ተገለጸ፣
መረጃው ጨምሮ እያጋጠመ ላለው ችግር መፍትሄ እንዲደረግላቸው ኣቤቱታ ባቀረቡበት ግዜም የፅህፈት ቤቱ ሓላፊዎችና ግብር ኣስከፋዮቹ ተስማምተው ጉቦ ለመቀበል እንዲመቻቸው በማሰብ ቅዳሜ እና እሁድ መጥታቹ ክፈሉ ስለሚልዋቸው፤ ኣሰራሩ ለነጋዴዎቹ የሚያስቸግርና እረፍት የሚያሳጣ እንደሆነባቸው ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኣዲስ ኣበባ ከተማ የሚገኙ ኣውራ ጎደናዎች ለውሃ ማስተላለፍያ ትቦ፤ ለኤሌትሪክ መስመር፤ ለመንገድ ንጣፍ ስራና፤ ሌሎች ስራዎች እየተባሉ ከተቆፈሩ ቦሃላ በግዜው ተጠናቅቀው ለኣገልግሎት ብቁ ሳይሆኑ ለረጅም ግዜ ተዘግተው ስለሚገኙ፤ ነዋሪዎች ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሰው ዕለታዊ ስራቸው እንዳያከናውኑ ትልቅ እንቅፋት በመሆኑ ምክንያት ያካባቢው ነዋሪ መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ ኣክሎ እስረድተዋል፣:
via:demhitonline
No comments:
Post a Comment