ይህ ጽሁፍ በብሎምፎንቴን ቆይታዬ የመጨረሻዬ ነዉ፡፡አሁን የዋልያዉ አባላት እቃቸዉን ሸክፈዉ ለጉዞ ዝግጀት ላይ ናቸዉ፡፡የ10 ቀናት ቆይታ ማብቂያ ቀን ነዉ ዛሬ፡-አንድ ሰዉ ግን ከህይወቱ ጠላት ጋር ዛሬ ጦርነቱን ለመጀመር ከተማ ይቀይራል፡፡ለ15ቀናት ያህል በአንድ ክፍል አብሬ ያሳለፍኩት ባልደረባዬ ጋር ዛሬ እንለያያለን፡፡እሱ ህይወቱን ሊያሣጣዉ ተቃርቦ የነበረዉን በሽታ ለመዋጋት እዚሁ ደቡብ አፍሪካ ይቆያል፡፡ግን እንዲህም ታሞ ቢሆን ግዳጁን ጨርስዋል፡፡እየደከመዉ እንኳን 3ቱንም የዋልያ ጨዋታ ያስተላላፈ ታሪካዊ ሰዉ ሁንዋል፡፡ጨዋታዉን እያሥተላላፈ እጁ ይዝላል፡፡እግሩን በአንድ ቦታ ለረዥም ሰአት ማስቀመጥ ስለማይችልም ያንፈራጣዋል፡፡እንዳንዴም ይቆማል፡፡ከአቅም በላይ ሲሆንበት ስርጭቱን ለሰከንዶች አቁሞ እረፍት ይወስዳል፡፡እንዳልረዳዉ ፍቃድ አልተሰጠኝም፡፡እንዳልተወዉ ደግሞ የዋሁ የሥራ ባልረባዬ ነዉ፡፡እናም አብሮት የሚያሥተላልፍ ሰዉ ፍለጋ ተባበርኩት፡፡
መኳንንት በርሄ የተወለደዉ ጎንደር ከተማ ነዉ፡፡ስፖርት ከልጅነት እስከ እዉቀት በፍቅር የዘለቀበት መንገዱ ነዉ፡፡ኤፍ.ኤም 97.1ድን የተቀላቀለዉ 1999 ላይ ነበር፡፡የዛሬ አመት ዋልያዉ ሱዳን ጋር ተጫዉቶ ሲመለስ መኳንንት የሆነ የህመመም ስሜት ይሰማዋል፡፡”እኔ የመሰለኝ ወባ ነበር፡፡እናም ሀኪም ጋር ሄጄ የወባ መድሀኒት ዉሰድ ብሎኝ ወሰድኩ፡፡ህመሙ ግን አልቆመም፡፡ከቀናት በኋላ አክታዬ ቀለሙን መለወጥ ጀመረ፡፡አሁንም ሀኪሜ ጋር ሄድኩኝ፡–ዶክተሩ የአባቴ ዘመድ ነዉ፡፡እናም ደንግጥዋል፡፡ሌላ መድሀኒት ሰጥቶኝ ሊሄድ ስል ጓደኛዬ እግሩንም እኮ ያመዋል–እያበጠ ነዉ አለችዉ፡–”
ነገርየዉ ከዚህ በኋላ ከባድ ህመም መሆኑ ተደረሰበት፡፡የደም መርጋት በሰዉነቱ ዉስጥ ተፈጥርዋል፡፡ያለበት ሁኔታ ደግሞ አንድ ጤነኛ ሰዉ ሊኖረዉ የሚችለዉ የደም ዝዉዉር የልብ ምተ አደለም፡፡ስለዚህ በቀጥታ ወደ ቤተዛታ ሆስፒታል ድንገገኛ ክፍል እንዲገባ ዶክተሩ ወሰነ፡፡ከዚህ በኋላ መኳንንት ለ12 ቀናት በመኖር ና በመሞት መሀል የመቆያ ክፍል ዉስጥ አሳለፈ፡፡”ዶክተሩ ጓደኛዬን ህመሙ ከባድ እንደሆነ ሲነግራት ደነገጠች፡፡እንደዉም የመትረፍ እድሌ ጠባብ እንደሆነ ጭምር ሲያሳዉቃት ራስዋን መቆጣጠር አቃታት፡፡ከ13ቀናት በኋላ አገገምኩ፡፡ዶክተሩ ያላሰበዉን ነገር በማየቱ ተደነቀብኝ፡-መኳንንት አንተ የተረፍከዉ በፈጣሪ ቸርነት ነዉ አንጂ እንደኛ እዉቀት እና ግምት ሞተህ ነበር ያለኝን መቼም ቢሆን አልረሳዉም” በማለት ያንን ጊዜ ያስታዉሳል፡፡
የደም መርጋት በጊዜ ካልታከመ ለሞት ይዳርጋል፡፡ባለፈዉ ሳምንት እዚህ ብሎምፎንቴን የሚገኝ ሀኪም ቤት ለቼክ አፕ አብረን ሄድን፡፡ዶክተሩ የበሽታዉ ምክንያት ምን እንደሆነ ታዉቆ ለሱ የሚሆን መድሀኒት ከዛም ወዲህ ደግሞ በሽታዉ ተመልሶ እንዳይመጣ የሚያደርግ ህክምና እንደሚያሥፈልገዉ አረጋግጦለታል፡፡”እንግዲህ መኳንንት በርሄ ከደቡብ አፍሪካ” የሚለዉን ዜና በቲቪ እና ሬድዬ ሲልክ መኳንንት በህመም ስቃይ ዉስጥ ሁኖ ነዉ፡፡ድንገት ፊቱ ይጠቁራል፡፡እግሩንም ያመዋል፡፡የግራ እግሩ ከቀኝ አግሩ በ5ት ሴንቲ ሜትር ይወፍራል፡፡በወጣትንት እድሜ ላይ ይህ አይነቱ በሽታ ሰለባ በመሆኑ ደግሞ ይሰማዋል፡፡
ከፍተኛ ህክምና እንደሚያስፈልገዉ ካወቀ ጀምሮ መኳንንት እንቅስቃሴዎችን አድረጎ ነበር፡፡የባህሪዉ ቁጥበነት እንዳለ ሁኖ የጋዜጠኞች ማህበርን ስለ ጉዳዩ አሳዉቆ መፍትሄ ጠይቆ ነበር፡፡በስፖርት ጋዜጠኞች ስም የሚጠራዉ ማህበር ግን ምንም አላደረገለትም፡፡በዚህ መኳንንት ከፍተኛ ቅሬታ አለዉ”ህመሜን ለብዙ ሰዉ ስደብቅ ይተባበረኛል ብዬ ለማስበዉ ማህበር ተናግሬ ነበር፡፡አሁንም አሁንም ለአመራሮቹ ችግሬን ብነግራቸዉም ምንም ነገር አላደረጉልኘም፡፡እኔ በነሱ ቦታ ብሆን ነገሮች ቀላል እንደሚሆኑልኝ አቃለሁ፡፡ከግለሰብ ይልቅ ማህበር ተሰሚነት አለዉ፡፡አለመታደል ሁኖ ግን የኔን ጉዳይ ከቁብ አልቆጠሩትም፡፡በዚህ በጣም አዝኛለሁ፡-እኔ የማህበሩ አባል ለመሆን መጀመሪያ በህይወት መቆየት እንዳለብኝ ማንም ያቀዋል፡-ከአባልነቴም እራሴን ስለማግለል እያስበኩኝ ነዉ”ብሎኛል፡፡የጋዜጠኞች ማህበር መግለጫ ከማዉጣትና የዉጪ ጎዙ ከማሳካት ዉጭ እንዲህ አይነቱ ነገር ሲደር ግንባር ቀደም ደራሽ መሆን ነበረበት የኔም እምነት ነዉ፡፡
ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ የዚህ በሽታ ህክምና ይገኛል፡፡ዋጋዉ እሰከ 350ሺ ብር ይጠጋል፡፡በዚህ ቀዉጢ ወቅት የዋልያዎችን ጨዋታ በህመም ስሜት ዉስጥ ሁኖ እንኳን ወደ ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ያደረሰዉ ጋዜጠኛ ድጋፍን ይሻል፡፡50 ሎሚ ለ1 ሰዉ ሸክሙ ለ50 ሰዉ ጌጡ አደል አባባሉ!!!
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ከቦታዉ በቀጥታ በማስተላለፍ የተሳተፉ ጋዜጠኞች ቁጥር 5 ነዉ፡፡መኳንንት 3ቱንም ጨዋታዎች ለብቻዉ በማስተላለፍ ዜናዎቸንም በማድረስ ወሳኝ ሚና ነበረዉ፡፡ለ15 ቀናት የደቡብ አፍሪካን ዝግጀት የዋልያዉን ዉሎ በአብሮነት አሳልፈናል፡፡ዛሬ ግን እሱ ወደ ህክምና ዋልያዉ ወደ ቤቱ ሊመለስ ነዉ፡፡እናም መኳንንትን ልሰናበተዉ ግድ ይለኛል፡፡በምኞት ብቻ ግን አደለም ከአጠገቡ እንደምንሆን ቃል በመግባትም ጭምር፡— ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ..የባንክ ቁጥር
No comments:
Post a Comment