Monday, September 9, 2013

ጫት ከየት እንደተገኘ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?፤ የጫት ወግ እና (የሀረር ተረት)

Source:ከአፈንዲ ሙተቂ

ጫት ከየት እንደተገኘ ማወቅ ትፈልጋላችሁ? እንዲያ ከሆነ አንድ የሀረሪመለሳይየነገሩኝን ጣፋጭ ወግ እንካችሁ ልበላችሁ (“መለሳይሲባልጨዋታ አዋቂመለኛብልሃተኛእንደማለት ነው-በሀረሪ ቋንቋ)፡፡
ኢስከንደር (እስክንድር/አል-ኢስከንደር/አሌክሳንደር) ይባላሉ፡፡ እዚሁ ምስራቅ ኢትዮጵያ ነው የኖሩት፡፡ የመሬቱን ዓለም ሁሉ በእግር በፈረስ አዳርሰውታል፡፡ አንድ ያላዩት ቦታ፤ ያልጎበኙት ሰፈር የለም፡፡ የምድሩ ሲሰለቻቸው የሰማዩን ለማየት ተመኙ፡፡ ግን በምን ይውጡ፡፡ መሰላል የላቸው፣ ክንፍ የላቸው፣ አስማት የላቸውበምንይሞክሩት እንግዲህ?
ድንገት ተኝተው ሲያስቡ አንድ ብልሃት ታያቸው፡፡ለምን ባዝራ ፈረሴን በንስር አሞራ አላስጠቃትም? ክንፍ ያለው ውርንጭላ አትወልድልኝ ይሆን?” አሉና ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ በነገሩ ሲያስቡ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን ውጥኑን ለመተግበር ቆርጠው ተነሱ፡፡ እንዳሰቡትም ባዝራቸውን በንስር አስጠቁ፡፡ ባዝራዋም ምን የመሰለ ባለ ሁለት ክንፍ ቦራ ፈረስ ዱብ አደረገች፡፡
ኢስከንደር ግለገሉን ስጋ ብቻ እየመገቡት አሳደጉት፡፡ ከዚያ የተወጠነው ሊተገበር ተወሰነ፡፡ ወደ ሰማይ መውጣት! እውነትም ቻሉበት፡፡ ይህ እንዴት የሆነ መሰላችሁ?
ፈረሱ ስጋ ብቻ ነው የሚባለው ብዬም አይደለም? ግን ሲጋልብ እንዳሻው ነው፡፡ ቢፈልግ መሬት ላይሳብ ሳብ..” ይላል፣ ቢፈልግ አየር ላይ ይበራል፡፡ ኢስከንደር ወደ ሰማይ መውጣት ሲፈልጉ ኮርቻው ላይ ወጡና ኮረኮሩት፡፡ ፈረሱ አየር ላይ መብረር ጀመረ፡፡ ኢስከንደር በእንጨት ላይ የተሰቀለ ስጋ ከፊቱ አንጠለጠሉለት፡፡ ፈረሱ ስጋውን አገኘሁት ሲል ኢስከንደር እንጨቱን ወደ ሰማይ ከፍ አደረጉት፡፡ ፈረሱ ስጋውን ለማግኘት እንደገና ወደ ሰማይ ብርር! ኢስከንደርም ስጋውን ከፍ! ፈረሱ ስጋውን ለማግኘት ወደ ሰማይ ብርር! እንደገና ኢስከንደር ስጋውን ከፍ! ፈረሱ ብርር
ከዚያ የት ይደርሳሉ መሰላችሁ?…. “ጀንነት” (በክርስቲያኖች እይታ መንግሥተ ሰማያት)!!! አቤት ሽታዋ... አቤት አጸዷ! ኢስከንደር ለዚህ ያበቃቸውን አምላክ እያመሰገኑ ከፈረሳቸው ወረዱ፡፡ ስጋውን ጣሉለትና በጀንነት ቁጥቋጦ ላይ እንደነገሩ ሸብ አደረጉት!! ከዚያም የጀንነት ጉብኝታቸውን ጀመሩአዩት ፍራፍሬውን! ቱፋህና ኢነቡን! ተምርና ዘይቱኑን! በጨፌዋ ላይ እየተራመዱ ሲያደንቁት ዋሉ፡፡

በድንገት ግን የጀንነት መሌይካ (መልአክ) መጣባቸው! አቤት ግዝፈቱ! አቤት ክንዱ! አቤት ዐይኑ! ኢስከንደር ፈሩት! መሌይካው ሳይዛቸው ወደ ፈረሳቸው በረሩ፡፡ ከታሰረበት ቁጥቋጦ እንኳ ሳያላቅቁት ከኮርቻው ላይ ጉብ አሉበት፡፡ አንዴ ቢኮረኩሩት ፈረሱ ወደ መሬት ብርርር አለ! ኢስከንደር ልባቸው እንደ ከበሮ እየመታ ከቤታቸው ደጃፍ ደረሱ፡፡ተመስገን አሉ!” አሉ ኢስከንደር:: “ሳይቸግረኝ ሰማይን አያለሁ ብዬ ያለ ጊዜዬ ልሞት?” አሉ ተጓዡ ኢስከንደር፡፡

ከዚያም በረዥሙእፎይብለው ፈረሳቸውን ሊያስሩ ገመዱን ዘርጋ ሲያደርጉት በጀንነት ውስጥ ከታሰረበት ቁጥቋጦ የተቀነጨቡ አራትሀባቅጠሎችን አገኙበት፡፡ ቅጠሉን ቢያዩት ከዚያ በፊት የማያውቁት ዐይነት ነው፡፡ እስቲ ከበቀለ ልሞክረው አሉና ከጓሮአቸው ውስጥ ወረወሩት፡፡ ከሶስት ወር በኋላ ምን የመሰለ ለምለም ተክል!! ኢስከንደር ከተክሉ ቅጠሎች ላይ ቀንጥሰው ሞከሩት፡፡ አቤት ሲያጫውት! አቤት ሲያስጨፍር! አቤት ሲያስደስት! አቤት ሲያመረቅን! ሂልዋ! ሰላም! ሰላም!

በዚህን ጊዜም ኢስከንደርሰው ሁሉ እየቀነጠሰው ጨዋታውን ያሳምርበት ዘንድ ይህንን ውድ ተክልጫዋትብዬዋለሁአሉ፡፡ ስያሜው እኛ ዘንድ ሲደርስጠፍታለትጫትብቻ ሆነና ቀረ፡፡ ወዳጄ! እንግዲህ ጫት እንዲህ ነው የተገኘው፡፡ ለኢስከንደር ትልቅሰዋብእየለመንን ጫታችንን እንቃም፡፡
--------
(ሀረሪዎች የመጨረሻውን አንቀጽ አያውቁትም፡፡ መደምደሚያው ያምር ዘንድ እኛ ነን የጨመርንበት፡፡ ለዚህም ከፍያ አንጠይቃችሁም፡፡

በነገራችን ላይእኛማለትን ለጃንሆይ ያስተማርነውእኛነን፡፡ ስለዚህ የጃንሆይን አባባል ሰረቃችሁ ብላችሁ የኮፒራይት ጥያቄ አታንሱብን)፡፡

No comments:

Post a Comment