Sunday, September 29, 2013
«አስተዳደሩ አዞናል። እባካችሁ ችግር ዉስጥ አትክተቱን»በሚል ፖሊሶች ልመና አድርገዋል። የአገዛዙ ፓርቲዎች ተደብቀዉ ህዝቡን እና ፖሊሲን ለማጋጨት እየሞከሩ ነዉ።(Minilik Salsawi)
«አስተዳደሩ አዞናል። እባካችሁ ችግር ዉስጥ አትክተቱን»በሚል ፖሊሶች ልመና አድርገዋል። የአገዛዙ ፓርቲዎች ተደብቀዉ
ህዝቡን እና ፖሊሲን ለማጋጨት እየሞከሩ ነዉ። ግን የአንድነት አመራሮች በአገዛዙ ወጥመድ ዉስጥ ላለመግባት በማስተዋልና
በእርጋታ ሕዝቡን እየመሩት ነዉ።
«ሃሩር የሆነ ጸሃይ ነዉ። ሕዝቡ ሂድ ስንለው ይሄዳል። ተቀመጥ ስንለው ይቀመጣል። በጣም ጨዋና ሰላማዊ ህዝብ ነዉ።»
አቶ ሃብታሙ አያሌዉ
የሕዝብ ማእበል – ፖሊስ ሕዝቡ ሰልፍ እንዳይቀላቀል ሲያከላክል
መፈክሮች !
ሕዝብ አሸማቆ መግዛት አሸባሪነት ነዉ !
ኢሕአዴግነት ከኢትዮጵያዊነት አይበልጥም!
አንድ ናት አገራችን !
ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ነዉ !
መብታችንን ከኢሕአዴግ አንጠብቀም !
ይሄ ስርዓት እስኪለወጥ ትግላችን ይቀጥላል።
ዶር ነጋሶ «ከቀበና ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል አድርገን ወደ ጃን ሜዳ እንድንቀሳቀስ ነዉ የሚፈልጉት። ይሄ ደግሞ
አይሆንም።አደባባዩን ለመዞር እየሞከርን ነዉ። ከዚያ ወደ አራት ኪሎ እንዞራለን። ከፖሊስ ጋር ለመደባደብ አንፈልግም። እኛ
ሰላማዊ ነን። » ዶር ነጋሶ የአንድነት ሊቀመንበር
«ይሄን ሰልፍ ፖሊሶች እየዘጉት ያለዉ በአስተዳደሩ ቀጥተኛ ትእዛዝ ነዉ። ተጠያቂዉ አስተዳደሩ ነዉ» አቶ ዳንኤል ተፈራ።
ቋጠሮ ፣ አቡጊዳ፣ ዘሃበሻ ፣ ኢትዮጵያን ሪቪው ድህረ ገጾች በአሁኑ ጊዜ አገር ቤት የሚደረገዉን ሰልፍ በስፋት እየዘገቡት ነዉ።
የቃሌ፣ ሲቪሊቲ፣ ከረንት አፌር የፓልቶክ ክፍሎችም በቀጥታ ከአዲስ አበባ ስልክ እየደወሉ ሰልፉን እያስተላለፉ ነዉ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment