Friday, September 27, 2013

እንደ አልባራዳይ ብርታቱን ይሰጠን (ከሎሚ ተራ)

4 hours ago by  0

MESKEL2
27/09/13
አድነነ ከመአቱ: ከሻአቢያ እና ከ7ቱ ። ተመሰገን ደሳለኝን አመሰግኜ ነው ዛሬ መጣጥፌን የምጀምረው። ይገርማል የሰሞኑ ሐሳቤና ጭንቀቴ የነበረው በርግጥም ሰለወያኔ ሥረአት ማክተም ሳይሆን፤ ወያኔ ከተወገደ በሖላ ምን አይነት ሰርአት ነው ሊመሰረት የሚችለው ? የሚለው ነበር። በተለይ ከሻአቢያ ጋር የማበር አባዜ ከተነሣ ወዲህ እረፍት አልሰጥ ብሏኛል። ታዲያ ይህንኑ ሳወጣና ሣወርድ አድሬ፤ እንደወትሮዬ ማልጄ ተነሰቼ ድሕር ገጾችን ሰመለከት የተመሰገን ደሳለኝን ” ከለውጡ በሖላሰ ?” በሚለው ፅሁፉ እሰካሁን የተወጣበትንና የተወረደበትን የፖሎቲካ ድርጅቶችን እንቅሰቃሴ በቅጡ ከገመገመ በሖላ፤ የወያኔ ውድቀት አይቀሬነቱን አረጋግጦ ከሚመጠው ለውጥ ባሻገር ሊደረጉ የሚገባቸው ናቸው ብሎ ያላቸውን ጠቃሚ ነጥቦቸ ጠቆም ጠቆም አድርጓል ልብ የሚል ልብ ይበል ነው ነገሩ።
እኔም በተመሰገን መጣጥፍ ከሞላጎደል የምሰማማበትና በተለይም በመጨረሻው ሃሳቡ “እንደ አልባራዳይ “ የሚለውን ለመጋራት ነው። ከሻአቢያ ጋር ሕብረት ከሚለው“ከመ አቱ ፤ ከ7ቱ “ ሃሣብ መቶ በመቶ የተሻለና የሚደገፍ ነው ብዬ ሰለማምን ነውና የሚሻልበትን ብዙም ሃተታ ሣላበዛ እንደተለመደው በ 2 ሀሳብ ጥንታዊ በሆኑ ተረታዊ አባባሎችን መንደርደሪያ እያደረግኩ ነጥቦቼን ላሰቀምጥ። ምክነያቱም ነገር ቢበዛ በአኸያ አይጫንምና ነው።
ሆኖም አሁንም አንባቢያንን በአክበሮት የምለምነው፤ ያገር ጉዳይ ሆኖ የሻአቢያ ነገር አልዋጥልኸ ብሎኝ እንደዜጋ የዲሞክራሲ መብቴን ተጠቅሜ የሚሰማኛን ሃሳብ ለማካፈል እንጂ፤ ወያኔንን የሚቃወሙና የሚታገሉን ወገኖቼን በምንም አይነት ሁኔታ ማንኛውንም ድርጅትም ሆነ ኢትዬጲያዊ ወገኔን የመቃዎም አባዜ ይዞኝ እንዳልሆነ በትህትና እንድትረዱልኝ አደራ እላለሁ።
1ኛ) “አዘለም አቀፈም ያው ተሸከመ ነው:”። እነዲሉ፤-
ጫካ ገብቶ ለመታገል መወሰንም ሆነ ወደ አገርቤት በመመለሰ የሰላሙን ትግል መቀላቀል የቃላት ልዩነት ካልሆነ በሰተቀር ያው አይመሰላችሁም ? ዋናው ለመሞት መቁረጡ ላይ ነው ። ለምሳሌ ጂ7 በሻአቢያ እርዳታ ወያኔን ለመጣል ምሁራኖችም ጫካ ገብተዋል ? ብለው ሲሉ ያው በግልፅ እንደሚታወቀው ለመሞት ወሰነዋል አፈር ላይ ለመተኛት፤ አፈር ለመብላት ብሎም ወያኒ አሰኪወገድ በቆራጥነት መታገል መሆኑን ማንም ይረዳዋል። ታዲያ ከሻአቢያ ጎን ቆሞ በሕዘብ ልብ ከፈተኛ ሰጋት ከመጣል ? በእወነት ከቆረጡ የሚሊዎኖችን ልብ ከሰጋት በማዳን በሃገር ውሰጥ መሬት ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት እንደ ወጣት ታጋዬቹ የሚሊዎኖቹን አገራዊ ድጋፍ እያገኙ መታገል የተሻለ አይሆንም ትላላችሁ ? በርግጥ ተመሰገንም እንደጠቆመው ጂ7 በወያኔ የታገደና የተፈረደበት እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም ቅሉ read more
Via: Zehabesha

No comments:

Post a Comment