Thursday, September 19, 2013

ዋሊያዎቹ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ዋሊያዎቹ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው
Thursday, 19 September 2013http://www.ertagov.com
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በጥቅምት 3 እና በህዳር መጀመሪያ ለሚጠብቀው የናይጀሪያ ወሳኝ ጨዋታ ለዝግጅት የሚረዳውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ከጋናና ካሜሮን ጋር ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ሁለቱ ሀገሮች  ከኢትዮጵያ ጋር ለመጫወት ፈላጎት ማሳየታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ አቶ ታረቀኝ አሰፋ ተናግረዋል፡፡
ጋናና ካሜሮን ወቅታዊ ብቃታቸው ጠንካራ የሚባል በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ላለበት ወሳኝ ጨዋታ ክፍተቱን ለመሙላት ወሳኝ አጋጣሚ ይሆናል፡፡
ለወዳጅነት ጨዋታ የተመረጡት ሀገራት ከምዕራብ አፍሪካ መሆናቸው በአብዛኛው ከናይጀሪያ ጋር ተመሳሳይ የአጨዋውት ይዘት በመተግበር ለብሔራዊ ቡድኑ ሰፊ ልምድ እንደሚያካፍሉ ታምኖበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርግ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡     
የአቋም መለኪያ ጨዋታው መቸ እንደሚደረግ በትክክል ባይታወቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን ነገ  እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ከድልድሉ በኋላ ናይጀሪያን አሸንፈው ታሪክ ለመስራት መነሳሳታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
በአንጻሩ የናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኢትዮጵያን በቀላሉ አሸንፈው እንደሚያልፉ ቢናገሩም ንግግራቸው በአሰልጣኝ ስቴፈን ኬሽ አልተወደደላቸውም፡፡
“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን አቅለን ወደ ሜዳ አንገባም፣ እነርሱ እዚህ የደረሱት ጠንክረው በመስራታቸው እንጅ በስህተት አይደለም ሲሉ ስቴፈን ኬሽ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
በአዝመራው ሞሴ

No comments:

Post a Comment