ሐራ ዘተዋሕዶ. | January 16th, 2014
የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲኾን የሚጠይቁት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ከአንድ ሚልዮን በላይ አጠቃላይ ብዛት ያላቸውን የሀ/ስብከቱን ወጣቶች የሚወከሉና ከ140 ሰንበት ት/ቤቶች የተውጣጡ ናቸው፡፡
- በሀ/ስብከቱ፣ በክፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መዋቅርና አደረጃጀት ውስጥሰንበት ት/ቤቶችን በማደራጀትና በማጠናከር ተልእኳቸውን እንዲወጡ ማድረግ ከዋነኛ ዓላማና ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡
- የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ በማፋጠን፣ የቤተ ክርስቲያንን ኦርቶዶክሳዊ ማንነትና አስተዳደራዊ አንድነት በመጠበቅ፣ አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን በመከላከል፣ ሞያዊ አስተዋፅኦን ለቤተ ክርስቲያን የማበርከት ድርሻ ያላቸው የአያሌ ተሰጥኦዎች ባለቤት የኾኑ ሰንበት ት/ቤቶች በአባቶች እግር ላላቸው የተተኪነት ሚና ተጨባጭና ቀጣይ እንዲኾን ዋስትና ነው፡፡
- የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነዱ በፋይናንስ ፖሊሲውና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው÷ የቤተ ክርስቲያናችን የገንዘብ አያያዝና አሠራር ግልጽነትና ተቀባይነት ያለው እንዲኾን ማድረጉ መሠረታዊ ተልእኮዋን ለማጠናከር ከሚኖረውአጠቃላይ ፋይዳ ባሻገር በዋና ተግባርነት ደረጃ ያስቀመጠው የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት የሙዓለ ንዋይ ምደባ (budgeting or financial arrangements) በቂ የፋይናንስና በጀት ድልድል እንዲያገኝያስችላል፡፡
- ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ምሥረታ የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚጠቁመው 65 ዓመታትን ባስቆጠረው የዘመኑ የሰንበት ት/ቤቶች አሠራር የታቀፈው ወጣት 70% የምእመኑን አጠቃላይ ድምፅ ይወክላል፡፡
No comments:
Post a Comment