Sunday, January 12, 2014

የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር ጨመረ!!

ካሜራ ማን ደመቀ የተያዠበት መንገድ አሁንም ድረስ ይገርመኛል፡፡እሱ የያዠዉን አክሪዲቴሽን የያዙ ጋዜጠኖች ገብተዋል፡፡ነገር ግን ከአንድ ቀን በፊት የታሰሩት ጋዜጠኞች ወሬ ግን ፍርሀቱን አብሶበታል፡፡እናም በዚህ መሀል ስራዉን ይሰራ ነበር፡፡የአቀባበሉ ፎቶ እንዳያመልጠዉ አሁንም አሁንም ቀጭ ቀጭ ያደርጋል፡፡እናም ወደኛ ጋ ቀረብ ሲል አወራሁት፡፡መያዝ ኬጀመረ ፎቶ እያነሱ ማለፍ አማራጭ አንደሆነ አወራን፡፡እሱም ሚግሬሽን ላይ ሲደርስ እሱን አድርጎ አለፈ፡፡ዞር ብለን ስናይ ደግሞ ነገሮች ጥሩ ሁነዉ የተቀሩት ጋዜጠኞጭም ጭምር አልፈዋል፡፡እንደገና ወደ ኋላ ተመልሶ መግቢያ ሊያስመታ ሲሄድ ተያዠ፡፡
ፍቅሩ ተፈራ አብሮ ከቡድኑ ጋር ነበር የመጣዉ እናም በብር ሁሉም ነገር ያልቃል አለ፡፡ሂዶም ሰዎቹን አናገራቸዉ፡፡ከቆይታ በኋላ ነጎች ሊለዉጡ አልቻሉም፡፡አማባሳደሩም እዛዉ ነበሩ እናም ምንም መደረግ አልተቻለም፡፡ደመቀ እዛዉ እስር ቤት ቀረና ትላንት ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡
ትላንት ወደ ጆበርግ የመጣዉ የፌደሬሽን ካሜራ ማን እንደነገረኝ 5ተኛ ጋዜጠኛ በኢሊቨር ታምቦ አየር መንገድ ተይዞ ታስርዋል፡፡የቴሌቪዠን ጋዜጠኛዉ ኤፍሬማ የማነ በቅርቡ የዋልያዉን አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ዶክመንተሪ ፊልም ሰርትዋል፡፡እናም ወደ ቻኑ ዉድደር በአክሪዲቴሽን ሲመጣ ተከልክሎ በእስር ቤት ይገኛል፡፡ምናልባትም ዛሬ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ እንደሚችል ይገመታል፡፡
የካፍ ተወካዮችን እዚህ የዉድድር ቦታ ላይ ስለነገሩ አጥበቄ ጠየክዋቸዉ፡፡የሚድያ ቻነሉ ተወካይ ኬኒዲ ዙምባቢያዊ ነዉ፡፡”አክሪዲቴሽን ቪዛ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ አለ፡፡የማይሆንበትም እንደዛዉ…ምከንያቱም በደቡብ አፍሪካ ብዙ ኢትዮያዊያን እየመጡ ይቀራሉ፡፡ስለዚህ የደቡብ አፍሪካ ሚግሬሽን የካፍን አክሪዲቴሽን ባይቐበል ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ስለዚህ ቪዛ ማግኘት የግድ ነዉ፡፡በአንዳንድ ሀገራት አሰራር አክሪዲቴሽን እንደ ቪዛ አያገልግልም የሚል መልስ ሰጥኞል፡፡”
ነገር ግን ከተመለሱት ጋዜጠኞች መሀል አብዛኞቹ ከዚህ በፊት ለአለም ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ የመጡ ነበሩ፡፡በዛዉ በአክሪዲቴሽኑ…አሁንም እንኳን ከመጡት መሀል በወረቀቱ የገቡ መገኘታቸዉ ሚግሬሽኑ ወጥ የሆነ አሰራር እንደሌለዉ ማሳያ ነዉ፡፡
source:http://www.ethiotube.net

No comments:

Post a Comment