ተቃዋሚ ነኝ ባዩ ቡድን ይቅርታ ለመጠየቅ የተገደደው፣ የቡድኑ ሰብሳቢ የኾኑት የኮተቤ ደብረ ጽባሕ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ተቃውሟችን ከመዋቅር ጥናቱ እንጂ አቡነ እስጢፋኖስ ይነሡልን የሚል ጥያቄ የእኛ አይደለም›› በሚል ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በፓትርያርኩና በስምንት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፊት በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ላይ ለተሰነዘረው መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከኹሉ ቀድመው ሊቀ ጳጳሱን ይቅርታ መጠየቃቸው በቡድኑ አባላት መካከል የፈጠረው መከፋፈል ነው፡፡
‹‹የዘካርያስ እናት ሞተው ለልቅሶ ራያ በነበርንበት ወቅት የሀ/ስብከቱ አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊዎች [የለውጡ ደጋፊ መስሎ በርካታ አሻጥሮችን የሚፈጽመው አደገኛው ጉቦኛ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ] ደውለው÷ አቡነ እስጢፋኖስ አንተን ለመክሠሥ ከመዝገብ ቤት ሰነድ እያወጡብኽ ነው፤ ኃጢአት እየተፈለገብኽ ነው፤ ወኅኒ ሊከቱኽ ነው ስለተባልኹ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ስሜት የተናገርኹት ነው፤ የጠላ ሰው ብዙ ይናገራል፤ ብፁዕነትዎ አስቀይሜዎታለኹ፤ ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የሚመጥን ከእርስዎ የተሻለ ሊቀ ጳጳስ ከየት ይመጣል? በልጅነት የተናገርኹት ነው፤ የአባትነትዎ ይቅርታ ይደረግልኝ፡፡›› /የተቃዋሚ ነኝ ባዩ ቡድን መሪ ኃይሌ ኣብርሃ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ጫማ ላይ ወድቆ ከተናዘዘው/
የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ‹‹ከሓላፊነታቸው ይነሡ፤ ከሲኖዶስ አባልነት ይሰረዙ›› የሚለው ጥያቄ ኃይሌ ኣብርሃ ከምክራቸው ውጭ ያቀረበው መኾኑን በመጥቀስ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፊት ስለተናገረው የድፍረት ቃል በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ…
... click here to continue reading
No comments:
Post a Comment