Sunday, February 17, 2013

Woyanne Federal Police loot houses they are searching in the Bethel neighborhood of Addis Ababa

Residents in Addis Ababa's Bethel neighborhood are reporting that Federal Police troopers have been looting the homes they are searching since yesterday. The troopers, heavily armed and accompanied by dogs, are targeting Muslim homes. ስበር ዜና ከቤተል መንደር
ትላንት ቤተል አካባቢ ጭምብል ባጠለቁ እና የፍርድ ቤት የፍተሻ ፍቃድ ሳይዙ በየቤቱ እየገቡ ብርበራ ሲያረጉ በነበሩት የፌደራል ፓሊሦች በየገቡበት ቤት ያገኙትን ዋጋ የሚያወጡ ንብረቶችን ሲዘርፍ እንዳመሹ ተነገረ ::

በዚህ ህገ ወጥ ብርበራ ስም ለዘረፋ የተጋለጡ ሠዋች እንደገለፁት ፌ/ፓሊሦቹ በየገቡበት ቤት የተቀመጠ እና ቻርጅ ላይ ያለ ሞባይል በየመሣቢያ የተቀመጠ ወርቅ እና ገንዘብ ሲወስድ እንደ ነበር ተናግረዋል በግል ቦታ ድረስ ሄጄ ያነጋገርኩዎት 1እህቴ እንደ ገለፀችልኝ " ትላንት ከምሽቱ 4:30 አካባቢ በራችን ሲንኮክዎ ሄዳ እንድትከፍት የተላከችው ሠራተኛ ወደኛ የተመለሠችው ከምናውቀው ወዳጅ ጎረቤት ጋር ሳይሆን ቁጥራቸው ከ10 የሚበልጥ ጭምብል ካጠለቁ የፌደራል ፓሊሦች ጋር ነበር ይህን ስናይ ሁላችንም ደንግጠን ተነሳን ፌደራል ፓሊሦች ከአንድ ሰው በስተቀር ሁላችንም ወደ ውጭ እንድንወጣ ባዘዙን መሠረት ባለቤቴ ሲቀር ሁላችንም በ2ፌ/ፓሊሦች እየተጠበቅን ግቢ ውስጥ ቆምን ከባለቤቴ ጋር ቤት ውስጥ የቀሩት ፌ/ፓሊሦች ግን ብዙ ነበሩ ከ10 ደቂቃ በሆላ ብርበራ ጨርሰው የወጡት ፓሊሦች ጥቂት ጥያቄዋች ከጠየቁን በሆላ የሄዱ ሲሆን ወደ ቤት ከተመለስንና ትንሽ እንደ ተረጋጋን ባለቤቴ ስለ ሁኔታው ከአንድ ጎደኛው ጋር ለመነጋገር ሞባይሉን ቻርች ላይ ሠክቶ ከነበረው ቦታ አጣው ይህን ስናይ መዘረፋችንን አውቀንና ሁላችንንም ሌላ የጠፍ እቃዋች ካሉ ብለን ካያስቀመጥንበት ስንፈልግ የአንድ ልጄ ሞባይልና ከውጭ መጣ በእንግድነት እኛ ጋር ያረፈች የባለቤቴ እህት ቀን ለብሳው የዋለችው እና ፌ/ ፓሊሦች ከመምጣታቸው ከጥቂት ደቂቃ በፌት መኝታ ቤትዋ ኮሞዲኖ ላይ ያስቀመጠችው 20 ግራም የአንገት ወርቅ መጥፈቱን አረጋገጥን ከነጋ በሆላ የአካባቢው ሠው እንዴት ለሊቱ አለፈ ብሎ እርስ በእርሱ ለመጠያየቅ ውጭ የወጣ ሲሆን እኛ ቤት የተፈፀመው ዘረፋ በአብዛኛው ሙስሊም ቤቱም መድረሱን ተረዳን እኛ ላይ የደረሰ ደረሰ ለማንስ አቤት ይባላል ? ብለን ለአላህ ሠጠን ! ተቀምጠናል ይህ ብርበራ ሌላ ቦታ የሚደረግ ከሆነ ሰዋች እንዲጠነቀቁ ንገርልኝ " ብላ መልዕክትዋን ሰጣኝ ተለያይተናል
 
by MINILIK SALSAWI » Today, 15:1

No comments:

Post a Comment