Thursday, February 28, 2013

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያሪክ ኾኑ!!!


BEMjDN4CMAAmQwj.jpg large
የድምፅ ቆጠራው ውጤት ታውቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ አሸናፊ ! ! !
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – 98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – 98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – 70 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – 39 ድምፅ

ተመራጩ ፮ኛ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ
(ፎቶ ተስፋ ዓለም ወልደየስ)
በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚሾሙ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ይኾናሉ፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት !!!
በዛሬው የመራጮች መዝገብ 80መራጮች ተመዝግበዋል፡፡
806 መራጮች መርጠዋል፡፡
አንድ የድምፅ መስጫ ወረቀት ባዶ ኾኖ በመገኘቱ ዋጋ አልባ (የማይቆጠር) ኾኗል፡፡
ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ንግግር አድርገዋየምርጫውን ውጤት እንደሚቀበሉ ገልጸዋ ፤ አያይዘውም ባስተላለፉት መልእክት፣  ‹‹ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ የተሰጠኝን አደራ ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋራ አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይኾናል ብዬ አምናለኹ፤›› ብለዋል፡፡
እሑድ በዓለ ሢመቱ ከተፈጸመ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ተመልክቷል፡፡
ለምርጫው በአጠቃላይ ብር 3,650,000 ወጪ መደረጉን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ተናግረዋል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው አራት ንኡሳን ክፍሎች ነበሩት – የመራጮች ምዝገባና ቁጥጥር፤ የሕዝብ ግንኙነት ንኡስ ክፍል፤ የሎጅስትክ ንኡስ ክፍል፤ የሒሳብና በጀት ንኡስ ክፍል ናቸው፡፡
ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተሳተፉት መራጮች፡- ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ፣ ብፁዕ አቡነ ራፋኤል፣ ብፁዕ አቡነ ቢነም፣ ብፁዕ አቡነ ቢሾይ፣ ብፁዕ አቡነ ሂድራ ሲኾን በታዛቢነት የተወከሉት ካሚል ሚሸል ናቸው፡፡ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ(ሲቲቪ) የምርጫ ውሎውን በቀጥታ ሥርጭት አስተላልፏል፤ ለበዓለ ሢመቱም ተመሳሳይ ሽፋን እንደሚሰጥ ተገልጧል፡፡
ራሳቸውን ሸሽገው የቆዩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በምርጫው የቀትር በኋላ ውሎ ተገኝተዋል፡፡
ከምርጫው ውሎ ጋራ የተያያዙ ተጨማሪ ዘገባዎችንና ትችቶችን ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን፡፡ ከሐራ ዘተዋሕዶ ጋራ ስለነበራችኹ ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

No comments:

Post a Comment