Wednesday, April 17, 2013

የጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ጉብኝት በአዉሮጳ


የጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ጉብኝት በአዉሮጳ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሽትራስ ቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ከአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳት ከማርቲን ሹልትስ ጋር ዛሬ ተወያዩ።ሁለቱ ባለሥልጣናት ከመወያየታቸዉ በፊት ባገኘነዉ መረጃ መሠረት፥ በዉይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት፥ ይዞታ፥ የፕረስ ነፃነት እና የአፍሪቃ ቀንድ ሠላም ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።አቶ ኃይለ ማርያም የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ለመጀሪያ ጊዜ በአዉሮጳ በሚያደርጉት ጉብኝት ነገ ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ከሌሎች የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገርም ቀጠሮ አላቸዉ።በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ሥለ ጉብኝቱ የሚያቀዉ እንደሌለ አንድ የኤምባሲዉ ባለሥልጣን አስታዉቀዋል።የብራሥልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ገበያዉ ንጉሤ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC


No comments:

Post a Comment