የክቡር ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፋዉንዴሽን መስራች ጉባዔ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነዉ፡፡ በጉባዔዉ ላይ 73 ሰዎች በድምፅ እንዲሁም ከ1000 በላይ ያለ ድምፅ እየተሳተፉ ነው፡፡
ለፋዉንዴሽኑ ማቋቋሚያ ሱዳን ሁለት ሚሊዮን ዶላር፤ ደቡብ ሱዳን አንድ ሚሊዮን ዶላር፤ ጅቡቲ 500ሺ ዶላርና ኡጋንዳ 300ሺ ዶላር ለግሰዋል፡፡
ባለራዕዩ ታላቁ መሪ መለስ የገበያ አክራሪነት በአለም ታዳጊ ሀገሮች ያስከተለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመተንተን የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት አስተሳሰብ አማራጭ በማቅረብ አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ በመሆናቸው ፋውንዴሽኑ እሳቸውን ከመዘከር ባሻገር ለህዝቦች ዘላቂ ጥቅም መረጋገጥ ወሳኝ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ባለራዕዩ ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ በጄኔራል ዌንጌት ትምህርት ቤት የላቀ ውጤት በማስመዝገባቸው ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ፋውንዴሽን ሽልማት ተበርክቶላቸው ነበር፡፡ በስማቸዉ የሚቋቋመዉ ፋዉንዴሽንም ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦችን በሽልማት እንደሚበረታታበት ተገልጧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ ቤተ-መጻህፍትና አስክሬናቸው በክብር የሚያርፍበት መናፈሻ እንደሚያስተዳድር በማቋቋሚያ አዋጁ 781/2013 ላይ ተደንግጓል፡፡
የፋውንዴሽኑ ገቢ ከለጋሽ አካላትና በውርስ ከሚደረግ ድጋፍ ከመንግስትና በራሱ ገቢ እንደሚደጎምም በአዋጁ ተካቷል፡
ጉባዔዉ እንደቀጠለ ሲሆን በቆይታዉ በአቶ መለስ ዙሪያ በተዘጋጁ ፅሁፎች ላይ ይወያያል፡፡
ሪፖርተር ከበደ ካሳ
No comments:
Post a Comment