Friday, April 12, 2013

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፍትህ ይሰጠን በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ


ሚያዚያ  (አራት) ቀን ፳፻፭ /
ኢሳት ዜና:- የአርብ ስግደትን በማስከተል ከአንድ አመት በላይ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብታችን ይከበር ጥያቄ፣ በዚህ ሳምንትፍትህ ፍትህበሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችፍትህየሚል ጽሁፍ የያዙ ወረቀቶችን በመያዝ ፍትህን ሲጠይቁ የዋሉ ሲሆን፣ ፍትህ አጥተው በእስር ቤት የሚሰቃዩ  መሪዎቻቸውን እጃቸውን በማጣመር በድጋሜ አስበዋቸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት በታዩበት በዛሬው ተቃውሞ ምንም አይነት ግጭት አለመፈጠሩን ለማወቅ ተችሎአል።
በአዳማ ፍትህ የጠየቁ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደብድበው እንዲባረሩ ተደርጓል። በእስር ላይ በሚገኙት ሙስሊም መሪዎች ላይ ምንም አይነት ጠንካራ የሰነድም ሆነ የሰዎች ማስረጃ አለመቅረባቸውን የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ። አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም እንዲሁ የመሪዎቹ የፍርድ ቤት ሂደት ነጻና ፍትሀዊ አይደለም በማለት አጠቃላይ ሂደቱን እያጣጣሉት ነው።

No comments:

Post a Comment