አስገድዶ መድፈርን ያጋለጡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኛ ጉዳይ
አንዲት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በተማሪዎች አገልግሎት ዲን ተደፈረች ስለተባለበት ወንጀል ለዶይቸ ቬለ መረጃ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ አቶ ደማስ ካሳ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ትዕዛዝ ከስራቸው እና ከደሞዝ ታገዱ።

ግለሰቡ በአንፃራቸው የተወሰደው ርምጃ ትክክለኛ አይደለም በሚል ለተለያዩ ፌዴራል አካላት አቤቱታ አቅርበዋል። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደዘገበው፡ በዩኒቨርሲቲው በመልካም አስተዳደር ጉድለት ችግር ላይ እንደሚገኝ በዩኒቨርሲቲው የተበተኑ፡ እንዲሁም፡ ለትምህርት እና ለኮምዩኒኬሽን ሚንስትሮች የተላኩ ደብዳቤዎች አሳይተዋል።
No comments:
Post a Comment