Saturday, January 26, 2013

ከአሜሪካ የህወሓት ሰላዮች ዛቻ

አሜሪካ የመሸጉ የሕወሐት ሰላዮች ዛቻና ማስፈራሪያ መሰንዘር ጀምረዋል። አልፈው ተርፈው «ክስ» እንመሰርታለን ብለዋል።
ለማስፈራሪያቸው የሚበረግግ ባይኖርም - ነገር ግን ነፃነት ባለበት አሜሪካ ያሉ የፍትህ አካላት በብርሃነ፣ ስብሃት፣ በረከት፣ አዜብ አሊያም ሽመልስ….የሚሽከረከሩ መስሎዋቸው ያለሃፍረት አንደበታቸውን ሞልተው ሲደነፉና ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ መታየታቸው …ምን ያክል የሞራል ድቀት እንደተጠናወታቸው ያሳያል። ባለፉት ወራት ከተሰነዘሩ ተራ ስድቦችና ዛቻዎች የትላንቱ ለየት የሚያደርገው ነጥብ ስላለ ነው፥ ይህችን መልክት ለመፃፍ የተገደድኩት። እነዚህ ሰዎች አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የመሸጉ የሕወሐት ሰላዮች እንደሆኑ ላሰምርበትእወዳለሁ። ከጀርባቸው ብርሃነ እንዳለ በግልፅ በአንደበታቸው አረጋግጠውልኛል። ዋናው አላማቸው ደግሞ « ሳንጋለጥ..ቀድመን እናሸማቅ፤..» ከሚል ከንቱ አስተሳሰባቸው የመነጨ ነው።


እናንተ በንፁሃን ደም የታጠባቹ ወንጀለኛ የብርሃነ ጀሌዎች፥ የፈለጋችሁትን ብትደረድሩ እናንተን ከማጋለጥ ወደኋላ የሚያፈገፍግ ብዕር የለም!! በአሜሪካ ተቀምጣችሁ ከምትፈፅሙት የስለላ ወንጀል ባሻገር ያለው የጀርባ ጉድፍ ታሪካችሁ ገና አልተነካም። ከአገራችን ባህል ውጭ በሚያሳፍር ፀያፍ ተግባር ተዘፍቃችሁ በሴት እህቶቻችን ላይ ስትፈፅሙ የነበረው የቡድንና የተናጠል የአመንዝራ -ሴሰኛ ድርጊታችሁ የማይታወቅ መስሎዋችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል። በመንግስት ቢሮዎች ጭምር ምን አይነት ርካሽ ተግባር ስትፈፅሙ እንደነበረ የተሟላ ማስረጃ እንዳለ ልትገነዘቡ ይገባል። የምታመልኳቸውና የምታገለግሏቸው አገር ቤት ያሉ አለቆቻቹ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ሌሊት ከተገናኙዋቸው በኋላ አንገታቸውን በሰይፍ ቀልተው እልም ካለ ገደል ውስጥ የጨመሩ አረመኔዎች እንደሆኑና እናተም የእነርሱ«ዱካ» ተከታዮች እንደሆናችሁ ተግባራችሁ ይመሰክራል። ይህና ሌላው የወንጀል ተግባራችሁ በዝርዝር ለአደባባይ የሚበቃበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ልታውቁት ይገባል። ትላንት በአገር ቤት የተጀመረው እናንተን የማጋለጥ ሂደት ከማስጨነቅ፡በገንዘብ ለመደለል ከመሞከር ባለፈ የፌዴራል ፖሊሶችን በማሰማራት የግድያ ሙከራ ፈፅማችኋል። ለረጅም ወራት ለአልጋ ብትዳርጉም… ለተለመደው አረመኒያዊ ተግባራችሁ የተንበረከከ እንዳልነበረ ሁሉ ዛሬም የሚንበረከክ እንደሌለ ልታውቁ ይገባል። በጣም የሚገርመው «ክብራችን ተነካ» ለማለት መዳዳታቸው ነው፤ ለመሆኑ ክብር ምን እንደሆነ ያውቁታል?..ለሌላው ክብር የሌለው ስለ ክብር አንስቶ መናገር እንዴት ይቻለዋል?..በአገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች ያፈሰሳችሁትና አሁንም የምታፈሱት የንፁሃን ደም …ክብር ያለው የሰው ልጅ እንደሆነአታውቁም?...ለነገሩ<ጥፋት> ብቻ ከተጠናወተው አዕምሮ ፥ ምንም መጠበቅ አይቻልም።

የዚህ መጣጥፍ መነሻ ወደሆነው ክስተት እንሻገር፤ በቅርቡ በወጣውና « ፍቅረኛሞቹ አዜብና ብርሃነ» በሚል ርዕስ ለንባብ ከበቃው ፅሁፍጋር በተያያዘ ነው፤ ትላንት ሐሙስ ጃንዋሪ 24 2013 ከምሽቱ8፡14 ሰዓት “ሎዮላ” ሆስፒታል ውስጥ እያለሁ በBlocked Number ስልክ ተደወለልኝ፤ ማንነቴን ካረጋገጠ በኋላ ..« ግርማ እባለለሁ» አለኝ፤ ..ማን አልከኝ?...ስል መልሼ ለማረጋገጥ ጠየኩት። « ግርማይ እባላለሁ» ሲል በትዕቢት አይነት መለሰ።(ልብ በሉ…ሁለት ስሞች ነው የነገረኝ).. ከንግግሩ ማለትም ከቃላት አጠቃቀሙ በመነሳት.. ማንነቱን ለመለየት አያስቸግርም።
ስለ አለቃው ብርሃነና አዜብ ከደሰኮረ በሁላ በቁጣ « ማነው የነገረህ?» ሲል ሊያስፈራራ ሞከረ።…ፍ/ቤት እንኳ የመረጃ ምንጭህን
አስገድዶ መጠየቅ እንደማይችል ያለማወቁ ብዙም አላስገረመኝም፤.የተለያየ ምልልስ አደረግን፤.ከዛም ጠንካራ ቃላት ከተለዋወጥን በኋላ « ማወቅ አለብህ » ያለኝን በዛቻ መልክ ሰነዘረልኝ፤ ብርሃነ ኪ/ማሪያም (ማረት) እንዲሁም የአዜብ ወኪሎች የሆኑ ክስ ሊመሰርቱ እንደሆነ ተናገረ። 
በበኩሌ ያለአንዳች ፍርሃት መልስ ያልኩትን ሰጠሁት፤ ስልኩንም ዘጋሁት። እናነተ በወንጀል የተጨማለቃችሁ፥ አንድ ልታውቁት የሚገባ ነገር ..ተግባራችሁን ከማጋለጥ የሚያፈገፍግ ብዕር እንደሌለና እንደማይኖር
በድጋሚ ልጠቁማችሁ እወዳለሁ!!..መረጃ ለሰፊው ወገን ማድረሱ ይቀጥላል!! 
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com – January 25, 2013

No comments:

Post a Comment