Thursday, January 17, 2013

የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ


የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን አገልግሎት እንዲያቆም አዘዘ

ኢሳት ዜና:- እንደ ቢቢሲ ዘገባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት  አዲሱ ቦይንግ ድሪምላይነር ለጊዜው  አገልግሎት እንዳይሸጥ በአሜሪካ አቪየሺን ባለስልጣን ታግዷል።ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
በመላው ዓለም ላይ 50 የሚሆኑ ቦይንግ ድሪም ላይነር እንዳሉ ያመለከተው የዜና አውታሩ ዘገባ፤የቴክኒክ ፍተሻ እስኪደረግ ድረስ የሁሉም አገራት ቦይንግ ድሪምላይነር ፍላግሺፖች አገልግሎታቸውን እንዲያቆሙ የዩ.ኤስ ፌዴራል አቪየሺን አሳስቧል።
አዲሱ ድሪም ላይነር ነዳጅ የመትፋት፣ የኮክ ፒት መስኮት መሰንጠቅ፣ የፍሬን እና የኤሌክትሪክ ብልጭታ የመፍጠርችግር እንደተስተዋለበትም ተገልጿል።
የአውሮፕላኑ <<ሊትየም አዮን ባትሪ>> የፍተሻው ዋነኛ ትኩረት መሆኑም ተመልክቷል።
ትናትን ረቡዕ በጃፓን  ቦይንግ ድሪም ላይነር ላይ የባትሪ ችግር አጋጥሞ አውሮፕላኑ ባስቸኳይ እንዲያርፍ መደረጉን <<ኦል ኒፖን ኤር ዎይስ>>የተሰኘው የጃፓን አየር መንገድ ሪፖርት አድርጓል።
በዓለም ላይ ቦይንግ ድሪም ላይነርን የሚጠቀሙ ስምንቱም አየር መንገዶች በዩ.ኤስ አቪየሺን ማሰሰቢያ መሰረት አገልግሎቱን ማቆማቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
እነሱም የጃፓን፣የአሜሪካ፣የቺሊ፣ የህንድ፣የኩዋታር፣የፖላንድና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች ናቸው።
በብድር 10 ቦይንግ ድሪም ላይነር የገዛችው ኢትዮጵያ፤ ከአፍሪካ ብቸኛዋ የድሪም ላይነር ባለቤት ነች።
አውሮፕላኖቹ አዲስ አበባ ሲገቡ ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደነበር ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የጃፓን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ላይ ያጋጠመው የቴክኒክ ችግር በኢትዮጵያዎቹ ላይ አውሮፕላኖች ላይ አለመከሰቱን ገልጾ፣ ለጥንቃቄና ለደህንነት ሲባል ላልተወሰነ ጊዜ በረራ ማቋረጡን ዘግይቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment