Ethiopia News and Views
Tuesday, July 23, 2013
በዓለም- የሴቶች ግርዛት ጨምሮአል
በዓለም አቀፍ ደረጃ 125 ሚልዮን ሴቶች እና ሕፃናት የግርዛት ሰለባ መሆናቸውን እና በሚቀጥሉት አስር ዓመታትም በዓለም ዙርያ ከ30 ሚሊዮን የሚበልጡ ሴቶች ለግርዛት አደጋ እንደሚጋለጡ የተመ ድ የህጻናት ድርጅት ፣ ዩኒሴፍ አስታወቀ። ዩኒሴፍ በ29 የአፍሪቃ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ላለፉት 20 ዓመታት ያካሄደው እና ትናንት ይፋ ያወጣው ጥናት እንዳስረዳው፣ በጊኒ፣ ጅቡቲ፣ ሶማልያ እና በግብጽ የሴት ልጅ ግርዛት በተለይ ተስፋፍቶ ይታያል። ጥናቱ ከተካሄደባቸው ሀገራት ነዋሪዎች መካከል በቁጥር ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም ይፈልጋሉ። የሴትን ልጅ ግርዛት በማብቃቱ ትግል ላይ ወንዶችን ማሳተፍ ለትግሉ መሳካት ወሳኝ መሆኑን የጥናቱ ውጤት አመልክቶዋል።
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment