Wednesday, July 10, 2013

ሰበር ዜና- የአንድነት አባላት ታግተው " እንደራደር" ተባሉ !!

መንግስታዊ ሽፍታነት በኢትዮጵያ 
-----------------
ኢህአዴግ መንግስታዊ ሽፍታነቱን ገፍቶበታል፡፡ ዛሬ ጠዋት በደሴ ከተማ የቅስቀሳ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ ከአዲስ አበባ የተጓዙትን የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ የሆነውን አቶ ወንደሰን ክንፈን በማገት “እንደራረር” በማለት ላይ ይገኛል፡፡ 
አግተው እንደራደር የሚሉት ሽፍቶች ናቸው፤ መንግስት አግቶ እንደራደር ሲል ሽፍታነቱን በአደባባይ መረጋገጡ ነው፡፡
አንድነት የፓርቲው ጽ/ቤት እስኪዘጋና አባላቱ እስርቤቶችን እስኪሞሉ ህዝባዊ ንቅናቀው ይቀጥላል፡፡ ፓርቲው ያነሳው ህዝባዊ ጥያቄ በመሆኑ የአንድነት አመራሮችና አባላት መስዋዕት ቢሆኑም ህዝቡ ትግሉን ከዳር እንሚያደርሰው አንጠራጠርም፡፡
ፍኖተ ነጻነት ሰበር በማለት ያሰራጨው ዜና

No comments:

Post a Comment