Thursday, July 25, 2013

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኦነግ አባልነት በተከሰሱ ላይ ብይን ሰጠ

*ወያኔ በኦነግ አባልነት የሀሰት ክስ አቀናጅቶ በግፍ ባሰረቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላይ በሚቆጣጠራቸው ዳኞችና አቃቢህጎች አማካኝነት ሽብርተኛ ናቸው በማለት የጥፋተኛነት ፍርድ አስተላልፏል።

በሽብርተኛነት ተፈርጀው ጥፋተኛ ከተባሉት ውስጥ አያሌ የአዳማ፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ እና የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።

*“በኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀ የሰብአዊ መብት ረገጣ መኖሩ ይታወቃል ይሁንና ለጋሽ ሀገሮች ይህንን ጉዳይ ከግምት ያስገቡ አይመስልም።” አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች
ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኦነግ አባልነት በተከሰሱ ላይ ብይን ሰጠ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በኦነግ አባልነት ተጠርጥረው ክሥ በተመሠረተባቸው ደቻሣ ዊርቱ፣ ጌቱ ሳቀታ እና ዓለሙ ተሾመን ጨምሮ በ21 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ብይን አሣለፈ፤ አንድ ተከሣሽ በነፃ አሰናብቷል፡፡

ችሎቱ ለፍርድ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሐምሌ 30/2005 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡


No comments:

Post a Comment