Tuesday, July 29, 2014

“ዶ/ር ኢንጂነር” ሳሙኤል ዘሚካኤል ኬኒያ ላይ ተይዞ ወደ ሃገር ሊመለስ ነው ተባለ

eng samuel z(ዘ-ሐበሻ) አነጋጋሪው ‘ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል’ ኬንያ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና ወደሃገር ቤትም እንደሚመለስ ኢቶሚካሊንክ የተባለው የራድዮ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ አስታወቀ።
በከተማው ውስጥ የማይገባውን የትምህርት ደረጃና ማዕረግ ጭኖ ሕዝብን ሲያታልል ነበር የተባለው ሳሙኤል ዘሚካኤል በመገናኛ ብዙሃን ድርጊቱ ከተጋለጠ በኋላ በርካታ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች በዚህ ሰው ተጭበርብረናል በሚል ክስ መመስረታቸው የታወቀ ሲሆን በኢንተርፖል አማካኝነት ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንደሚመጣ ይጠበቃል።
ራድዮው እንደዘገበው ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤል ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment