Wednesday, July 2, 2014

በረመዳን ጾም ወቅት በስፋት የሚበላው ቴምር ለጤና ያለው 10 በረከቶች

34
በዚህ የረመዳን ወር፣ ቴምር ይታወሳል። እስቲ ቴምር የሚከተሉት ጥቅሞች አሉትና ተገባበዙ። እኛም ምክሩን ጋበዝናችሁ።
ቴምር በቫይታሚን፣ ማዕድናትና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዲኖሩት አስችሎታል፡፡
1) ስብና ኮልስትሮል፦ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡
2) ፕሮቲን፦ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡
3) ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ሲሆን ፥ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 ን አካትቶ ይዟል፡፡
4) ሀይል እና ጉልበት፦ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡
5) ፖታሲየምና ካልሲየም፦ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ በመሆኑ በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ከመርዳቱም በላይ ፥ በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠንና ከፍተኛ ፖታሲየም መጠን በመያዙ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ያደርገዋል ፡፡
6) ብረት፥ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ለመታደግ ይረዳል።
7) ድርቀት፦ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
8) ሰውነትን ማጽዳት፦ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካል ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል – ቴምር !
9) ካንሰርና የዓይን ችግር፦ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ካንሰርን ለማከምም ተመራጭ ነው – ቴምር!
10) ቆዳ ችግር፦ ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና ያለው ሲሆን ፥ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡
Source: Admass Radio Atlanta
Source: Zehabesha

No comments:

Post a Comment