Thursday, March 6, 2014

ሀገር ማለት በትልቁ ሰዉ ነዉ...(ከመስፍን ሀ/ማርያም)

Mesfin Habtemariam
ሀገር ማለት በትልቁ ሰዉ ነዉ እንጂ ብቻዉን አፈሩ፤ ምድሩ፤ ተራራ፤ ወንዝና ሸንተረሩ አይደለም፡፡እንደሚታወቀዉ ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰቦች ሀገር፤ብዙ ቓዋንቓዋ፤ እምቅ ባህል እና ሀይማኖቶች ያላቸዉ ህዝቦች የሚኖርባት ሀገር ነች፡፡ የዚህ ሁሉ ጥቅል አንድን ሀገር ሀገር ያሰኛታል፤ የዚህ ሁሉ ራስ የሆነዉ ሰዉ ነዉ፡፡
 ይህንን ያልኮበት ምክንያት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነዚህን በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ህዝቦች ሲመሩ የነበሩ መንግስታት ወይም ነገስታት የሰሩወቸዉ አሉታዊ የሆኑ የታሪክ ጠባሳዎች አሉ፡፡ እነዚህ ጉዳት ደርሶብናል ብለዉ ጥያቄ ለሚያነሱ ወገኖች መብቶቻችንን ተነፈግን ኖረናል፤ እንደሰዉ ያልተቆጠርንበት ዘመን ነበር ብለዉ አሁን ለሚያነሱት ጥያቄ ጆሮ መስጠት እና ማዳመጥ ልዩንትን ለማጥበብ ኢትዮጵያቂነትን አንዲፈልጉ፤ አንደሚቀበሉና የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ያለበለዚያ ግን በማፈን ወይም በማግለል መፍትሄ ማምጣት አይቻልም፡፡ እኛ ዜጎች እንደ ሰለጠኑት ሀገራት የመደማመጥ የመከባበር እና የመደናነቅ ባህል ልናዳብር ይገባል፡፡
ሌላዉ የቀደሙት መሪዎች የሰሩዋቸዉ አወንታዊ የሆኑ በጎ ለሀገር የሚጠቅም ተግባራትን ከዉነዉ አልፈዋል፡፡ ስለዚህ አሁን ያለዉ ትዉልድ እነዚህን በጎ ጎኖች በማዳበር ስለወደፊት እጣፋንታችን ለመወሰን በጋራ በመወያየት የተሻለች ሀገር መገንባት የዚህ ትዉልድ ሀላፊነት ነዉ፡፡
የወያኔ መንግስት በዘራዉ መርዝ ተያይዘን እንዳንጠፋ በልዩነት የሚነሱትን ወገኖች ማዳመጥ ጥያቄያቸዉን ማክበር ለምንመኛት ወይም እንድትኖር ለምንፈልጋት ኢትዮጵያ ህልዉና ጉልህ አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡ ምክንያት ብጠቅስ ኢትዮጵያ የተገነባችዉ በዉሰጧ በሚኖሩ ብሄሮች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ህብረት ነዉ፡፡ ስለዚህ በዚች ሀገር ዉስጥ የሚኖሩ ህዝቦች እኩል በቅንልቦና ላይ የተመሰረተ የሁሉንም መብት የሚያስጠብቅ የጋራ ስርዓት መመስረት አሌ የማይባል ሀቅ ነዉ፡፡ ያለበለዚያ ግን መብቴ ይጠበቅልኝ፤ ማንነቴ የታወቅልኝ ብለዉ የሚነሱ የብሄር ጥያቄዋች ማፈን ዉጤቱ ለመለያየት፤ ለእርስ በእርስ ግጭት ምክንያቶች ከሚሆኑት ዉስጥ አንዱ እና ዋነኛዉ ነዉ፡፡
ስለአንድ ኢትዮጵያ ስናወራ ስለብዙሀኑ ብሄር ፍላጎት ማሰብ እና የመብት ጥያቄያቸዉን መመለስ የግድ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ስናደርግ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ሁላችንንም በአለም ፊት እኩል እና በልዩነታችን ዉስጥ አንድ እንደሆንን የምናሳይበትን እና ለቀጣይም ትዉልድ ሀላፊነታችንን ተወጥተን ከታሪክ ተወቃሽነት ልንድን እንችላለን፡፡ ያለበለዚያ ግን ”ዉሻ በቀደዳ ጅብ ይሾልካል” እንደሚባለዉ ይህንን ልናስወግድ ካልቻልን ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለተነሳዉ የጋራ ጠላታችን ወያኔ እንዲያፈራርሰን እና የምንኮራበት ማንነታችን እንዲጠፋ መሆኑ አይቀርም፡፡
ይህንን ሀላፊነት የማይሰማዉ የወያኔ መንግስት ከስልጣን ማስወገድ እና በወያኔ የጭቆና አገዛዝ እየተረገጠ ያለዉን ህዝባችንን ነፃ ማዉጣት ተቀዳሚ ተግባራችን አንዲሆን እግ/ር ይርዳን፡፡
ፍትህ ፈትህን ለተጠሙ ይሁን!!!
አስተያየት ለመስጠት፡Email: azu.mesfin@gmail.com
                              


No comments:

Post a Comment