Wednesday, March 12, 2014

ወያኔ በሁሉአቀፍ ትግል ከሥልጣን ይውረድ (መስፍን ከኖርዌይ)

ስርነቀል የፖለቲካ ስርአት ለማምጣት ወያኔ መራሹን መንግስት በሁሉን አቀፍ ትግል ከስልጣን ማዉረድ የግድ ነዉ፡፡
አሁን እንደሚታየዉ በሁሉም አቅጣጫ በኢትዮጵያ ዉስጥ አዲስ የፖለቲካ ለዉጥ እንድሚያስፈልግ እና ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት በወጣቱ ሀይል ላይ እየታየ ነዉ፡፡ ይህ የለዉጥ ፍላጎት እና መነቃቃት ወደኋላ እንዳይመለስ ትግሉ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡ በዚህ ረገድ በሀገር ዉስጥ በሰላማዊ መንገድ ወያኔን ከስልጣን ለማዉረድ እየታገሉ ያሉ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ምንም እነኳን የተለያየ የፖለቲካ ፕሮግራም(Ideology) ቢኖራቸዉም ይህንን ልዮነት ለጊዜዉ ወደኋላ ጥለዉ በጋራ በቅን ልቦናላይ በተመሰረተ መግባባት ህዝቡን የማነቃቃት፤ የመምራት እና የማደራጀት ስራን በመስራት የህዝብን አመኔታ እንዲየገኙ ማድረግ እና ከወያኔ (ከኢህአዴግ) የተሻለ አማራጭ ፕሮግራም አንዳለቸዉ በማሰየት የአገዛዙን ማንነት ባዶ ማሰቀረት ይችላሉ፡፡

ሌላዉ በዉጪ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የወያኔ አገዛዝ ያልተመቻቸዉ ዲያሰፖራ በጋራ ለዩነትን ባማስወገድ ቅድሚያ ለሚሰጠዉ የወያኔን አገዛዝ ከስልጣን ማዉረድ ላይ ሀገር ዉስጥ ከሚንቀቀሳቀሱት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት፡፡ አንደዚህ ልናደርግ ከቻልን በቀጣይ በ2015 ለሚደረገዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ የህዝቡን አወንታዊ ምላሽ አንዲያገኙ በማደረግ የወያኔን አገዛዝ፡ የስልጣን ዘመን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያከትምበት ይሆናል፡፡
እንደሚታወቀዉ የወያኔ መራሹ መንግስት በስልጣን ላይ እሰካለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ መከራ፤ እስራት፤ግድያ አንደዉ ባጠቃላይ ሁሉን አቀፍ ስቃይ፤ ችግር እንደ ሀገር የመቀጠላችን ጉዳይ አጠያያቂ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ የማፍያ አገዛዝ የየተኛዉንም ማህበረሰብ ዉክልና ሳያገኝ በጉልበት በመሳሪያ የሚቃወሙት ወገኖች ሲፈልግ አሸባሪ፤ ፅንፈኛና አክራሪ አያለ ስም እየለጠፈ በሀይል እያስፈራራ፤ እያሰረ፤ እየገደለ እና ከፊሉን ከሀገር አንዲሰደዱ፤ ለዘመናት ከሚኖሩበት እያፈናቀለ አነሆ 23 አመታትን አስቆጠረ፡፡

ስለዚህ በዚህ መንገድ ወያኔ መራሹን አገዛዝ በስልጣን ላይ እንዲቀጥል ልነፈቅድለት የምንችለበት እድል የለም፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለዉጥ ያስፈልገዋል፤ይህንን ለዉጥ ከማንም እና ማንም በችሮታ ሊሰጠን አይችልም፡፡ እኛዉ ራሳችን በተባበረ ከንድ ያለልዩነት እጅለጅ በመያያዝ ከታገልን ለዉጥ ማምጣት እንችላለን፡፡ ይህ ካልሆነ እና አሁን እንደሚታየዉ እርስ በእርሳችን የምንጠላለፍ ከሆን ለወያኔ እድል ፈነታ ከሰጠነዉ አሁንም መከራዉ፤ ችግሩ፤ ሰቆቃዉ በራሳችን ላይ እንደ ሚሆን ምንም ጥርጥር የለዉም፡፡ ይህ የህልዉና ጉዳይ ነዉ የመኖር እና ያለመኖር፡፡ ይህ እንደ ሃገር የመቀጠል እና ያለመቀጠል ጉዳይ ነዉ፡፡ ለነገ ብለን ጊዜ የምንሰጠዉ አይደለም፡፡

ሌላዉ አማራጭ ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ይለቃል ብሎ መጠበቅ የዋኽነት ቢሁንም እስከ መጨረሻ በሰላማዊ መንገድ ያሉትን አማራጮች ሞክሮ ካልተሳካ በትጥቅ ትግል ከአሁን ቀደም የጀመሩትን ሀይላት ድጋፍ በማደረግ ለዉጥ ማምጣት የግድ ነዉ፡፡ይህንን ሀላፊነት የማይሰማዉ የወያኔ መንግስት ከስልጣን ማስወገድ እና በወያኔ የጭቆና አገዛዝ እየተረገጠ ያለዉን ህዝባችንን ነፃ ማዉጣት ተቀዳሚ ተግባራችን አንዲሆን እግ/ር ይርዳን፡፡
በወያኔ አገዛዝ በጨለማ ዉስጥ ለሚማቅቀዉ ህዝባችን ብርሀን ይሁን፡፡
10.03.2014
መስፍን(ከኖርዌይ)
Source:http://www.ethiopianreview.com/amharic/?p=161751

No comments:

Post a Comment