|
ከመስፍን |
የአንድ ሉአላዊ ሀገር መንግስት ህዝቦቹን ከማንኛዉም አይነት ጥቃት ማስጠበቅ እና ደህንነታቸዉን ማረጋገጥ ከምንም በላይ
ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ተግባር ነዉ፡፡ ነገርግን ወያኔ ከዚህ በተቃራኒ ዜጎች በአረብ ሀገራት የሚደረሰባቸዉን ጥቃት
ቸል በማለትቱ ወንድም እና እህቶቻችን ደማቸዉ እንደ ጎረፍ በየመንገዱ ሲፈስ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ እጅግ የሚያሳፍር ተገባር ነዉ፡፡
እንደዉም ወያኔ በተቃራኒዉ ከሳዉዲ መንግስት
ጋር በመተባበር ወገኖቻችን ለስቃይ እንዲዳረጉ እያደረጋቸዉ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ፡፡ እነዚህ ወገኖች በስደት ባሉበት
ሳዉዲ አረቢያ መመለስ ካለባቸዉ አለም አቀፍ ህግ በሚፈቅደዉ መንገድ
ነበረበት፡፡ ነገርግን የሳዉዲ ፖሊሶች እና ዜጎቻቸዉ ተቆረቃሪ መንግስት ኢትዮጵያ ህዝቦቻ እንደሌላቸዉ ስላረጋገጡ ወገኖቻችንን እየገደሉ፤ እየደፈሩ እና እያሰቃዩዋቸዉ ነዉ፡፡
ሀገር የሚመራዉ ማፍያዉ መንግስት ወያኔ
ከሳዉዲ መንግስት ጋር በመተባበር ወገኖቻችንን እያሰቃየ
ነዉ፡፡ ዜጎች ከሀገር ዉስጥ በሰላም ሰርተዉ እንዳየኖሩ የ ወያኔ
ግፍ አገዛዝ አያማረራቸዉ በበወያኔ ደላላነት ወጣት ወገኖቻችን
ለዘመናዊ ባርነት ለአረብ ሀገራት አየተቸበቸቡ ይገኛሉ፡፡ የወያኔ የአገዛዝ ስርአት ዜጎችን ተስፋ በማስቆረጥ የኢኮኖሚ ጥገኛ እንዲሆኑ
ማድረግ ነዉ፡፡ ሁላችንም በኢትዮጵያ ዉስጥ የ ምንኖር ዜጎች ተዋረደናል
ሁለነተናችንን ወያኔ ለዉጪ ወራሪ አሳልፎ ሸጦናል፡፡ የወገኖቻችን ደም በአረብ ሀገራት ፈሶ አይቀርም፤ ወያኔም ሆን የሳዉዲ መንግስት
በዚሀ ጉዳይ ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡ የሳዉዲ መንግስት በ21ኛ ክፍለ ዘመን እንደዚህ አይነት ኢሰብአዊ የሆነ ተግባር በወገኖቻችን
ላይ በማደረሱ በጣም አዝነናል፤ አሳፋሪ ተገባር ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን የመብት ጥያቄ እንዳይጠይቅ ካደረጉ ምክንያቶች እና መፍትሄዎቹ ከብዙ በጥቂቱ፡
1.ህዝቡን በተለያዩ መንገዶች ትኩረቱን መያዝና ስለመብቱ፤ ስለኢኮኖሚ ብሎም ሀገሪቱ ዉስጥ
በመንግስት ስለሚደረጉ የጥፋት ተግባራት እንዳያወቁና እንዳይጠይቁ ማድረግ፡፡ በተለይ ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ወጣቱን ሀይል ከእዉቀት
እና ከኢኮኖሚ እንዲርቅ በማድረግ የተለያዩ ማዘናጊያዎችን በማመቻቸት፡- ለምሳሌ እንደ አዉሮፓ እግር ከዋስ፤ ጫት፤ ሺሻ፤ዘፈን በነዚህ ነገሮች በመያዝ መብቱ እስከምን
አንደሆነ እንዲረሳ እንዳይጠይቅ ማድረግ፡፡
2.የነፃ ሚዲያዎችን ማጥፋት እና በስመ ነፃሚዲያ ስም መንግስት በራሱ ቅኝት ጠፍጥፎ መስራት
እና የራሱን የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ እንዲሰሩ ማድረግ፡፡ ለምሳሌ፡ እነደ ዛሚ ኤፍም፤ሚሚ ስበሃቱ፣ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ !አዲስ አድማስ ጋዜጣ ...ወዘተ
3.መንግገስት የራሱን ሚዲያ በማብዛት በየለቱ ሙዚቃ እና እርባና የሌለዉ ለሃገር የማይተቅም
ወሬ በማዉራት የህዝቡን ስነልቦና መስረቅ፡፡ ምሳሌ ደቡብ ቲቪ፣አማራቲቪ፤ጋምቤላ ቲቪ፤አዲስ ቲቪ ወዘተ ግን ሁሉም አንድ ለናቱ ኢቲቪ
ግልገል ቲቪዎች ናቸዉ፡፡
4.ህብረተሰቡ ዉስጥ የስለላ መዋቅሩን በመዘርጋት እርስ በርሱ እንዳይተማመን በጥርታሬ እንዲተያይ
ማድረግ፡፡
5.በህዝብ ዉስጥ ሆን ብሎ አደገኛ የሆኑ ችግሮችን መፍጠር እና በፍጥነት አዉዳሚ የሆኑ መፍተሄዎችን
ማቅረብ፡፡ ለምሳሌ፡ የሽብር ጥቃት ሊከሰት ነዉ በሚል ሽብር በህዝብ ዉስት በመንዛት እራሱ መንግስት የሽብሩን ድርጊት መፈፀም፤
የሃይማኖት አክራሪነት ችግሮችን አጉልቶ ፕሮፖጋነዳ በመንዛት እና በማባባስ፤ ወግኡዝ በሀይማኖትም በባህልም የተባለለትን ግብረሰዶም
በሀገሪቱ ዉስጥ እንዲስፋፋ ማድረግ የመሳሰሉት
6.የከተሞች ምስቅልቅል ችግሮች እንዲያድጉ ማድረግ፡-ምሳሌ የዉሀ፣ መብራት፣ እና የትራንስፖርት ችግሮችን
ሆን ብሎ መፍጠር
7.ከባድ የሆኑ የኢኮኖሚ ችግሮችን መፍጠር ዋናዋና የሆኑ ፍጆታዎች ላይ ዋጋ መጨመር ወይም
እጥረት እንዲኖር ማድረግ
8.ህዝብ እዉቀት እንዳይኖረዉ
የጊዜዉን ቴክኖሎጂ እነዳያዉቅ ያደርጉታል፤ የተለያዩ website ችን እና social mediaችን በመዝጋት የኢንተርኔት አቅርቦትን ዝቅተኛ እዲሆን በማድረግ በመሳሰሉት ያዳክሙታል፡፡
9.ዝቅተኛ መደብ (Lower class)እና ከፍተኛ መደብ(higher class) በመፍጠር ተኩረትን ከመብት ወይም
ከፖለቲካ ጥያቄ በማስቀየር፤ ለመኖር በሚደረግ ትግል ብቻ አንዱ ገዢ መደብ ሌላዉን ደግሞ ተገዢ በማድረግ የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ
በማስቀየር የስልጣን ዘመናቸዉን ያራዝማሉ፡፡ ህዝብ ከተገዛ ባሪያ ነዉ፤ ከተዳደረ ግን ነፃ ነዉ፡፡ አሁን ኢትየጵያ ዉስጥ እየታየ
ያለዉ ማስተዳደር ሳይሆን መግዛት ነዉ፡፡ ምክንያቱም አሁን ኢትየጵያ ዉስጥ የሚታየ የአንድ ብሄር የበላይነት ነዉ፡፡ ለምሳሌ የጦር
ሃይሉን የሚመሩት ከአንድ ብሄር ከአነድ አምነት ነዉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች ከብዙ ጥቂተቶቹ ናቸዉ፡፡
ጠቅለል ባለ መንገድ መፍትሄ የሆናሉ ብዬ የማምነዉ
ወጣቱ ሀይል ላይ በስፋት እና በጥልቀት በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም የማንቃት ስራን መስራት፤ የህ ደግሞ በትልቁ የቤት ስራ
የሚሆነዉ በዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ነዉ፡፡ አንዴት ለሚለዉ እንደሚታወቀዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተለያዩ ዌብ ሳይቶችን፤ ብሎጎችን
መክፈት አይቻልም፡፡ ስለዚህ በሚቻሉ social mediaዎች(Cyber Technologies) በመጠቀም ወጣቱ ስለሀገሩ መረጃ አንዲደርሰዉ ማድረግ፤
የተለያዩ የፖለቲካ ideology የሚያራምዱ በዉጪም በሀገር ዉስጥም
ተቃዋሚ ድርጅቶች ቢኖሩም ልዩነታቸዉን ወደሓላ በማድረግ ቅድሚያ ለሚሰጠዉ ወያኔን ከስልጣን የማዉረድ ስራ ለመስራት መነሳት እና
ህዝብ እምነት እንዲጥልባቸዉ በማድረግ ከጎናቸዉ ማሰለፍ አለባቸዉ፡፡
በተለይ
በFacebook እነደ
ሚታወቀዉ ዉጤቱ ባያምርም በግብፅ እና ቱኒዚያ እንደ ተደረገዉ አንድ ጠንካራ የFacebook
ግሩፕ በመፍጠር በጋራ የማነቃቃት ስራን መስራት፡፡ ምክንያቱም አሁን
እንደሚታየዉ በጣም ለቁጥር የሚታክቱ የFacebook ግሩፕ
ስላሉ እነዚህን ወደ አንደ በማምጣት የተጠናከረ ስራ መስራት ስለሚቻል፡፡ ስንተባበር ሀይል ይኖረናል ስንለያይ ደግሞ ለወያኔ እድል
ፈንታ አንሰጠዋለን እና ነዉ፡፡
በዚህ መልኩ ጠንክረን እንስራ ወያኔን በቅርብ ከስልጣን አዉርደን የተጨቆነዉን ህዝባችንን መብት የምናስከብርበት ቀን ይፍጠን፡፡ አሜን