Friday, February 7, 2014

ሰበር ዜና/ፍኖተ ነፃነት- ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ

ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ 4 አመራሮችና አባላት እንዲታሰሩ ኢህአዴግ ወስኗል፤ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ታውቋል፡፡
*******************
ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment