Wednesday, February 12, 2014

‹‹ከረሃቡ ፅናት የተነሳ አንዳንድ ሰዎች ያገኙትን ነገር ይበሉ ነበር፡፡ ለእኛ እያንዳንዱ ቀን በሕይወትና በሞት ጠርዝ ላይ የተንጠለጠለ ነበር፡፡


ፍሬ ከናፍር

‹‹ከረሃቡ ፅናት የተነሳ አንዳንድ ሰዎች ያገኙትን ነገር ይበሉ ነበር፡፡ ለእኛ እያንዳንዱ ቀን በሕይወትና በሞት ጠርዝ ላይ የተንጠለጠለ ነበር፡፡ በሕይወቴ እንዲህ ዓይነት ቅስም ሰባሪ ነገር ያጋጥመኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡››
ይህ ልብ ሰባሪ ንግግር የተደመጠው ሰሞኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አማካይነት በከባድ መሣሪያ ድምጥማጥዋ ከጠፋው ሆምስ ከተባለችው የሶሪያ ከተማ በሕይወት የወጡት የ54 ዓመቱ ሶሪያዊ አቡ አብዱል ጀማል ነው፡፡ የቀድሞው የታክሲ ሾፌር በሶሪያ መንግሥትና በአማፂያን መካከል ላለፉት ሦስት ዓመታት በተካሄደው ዘግናኝ ውጊያ ምክንያት በሕንፃዎች ፍርስራሾች ውስጥ ተጎሳቁለው ይኖሩ ነበር፡፡ ከእሳቸው ጋር ሰሞኑን በረሃብ ምክንያት የከሱና በጣም የተጎሳቆሉ 250 ሶሪያውያን በሕይወት ተገኝተው ሲኦል ከምትመስለው ሆምስ ከተማ ወጥተዋል፡፡ አቡ አብዱል ጀማል በሦስት ዓመታት የሮኬትና የከባድ መሣሪያ ድብደባና ረሃብ ምክንያት የብዙዎች ቅስም መሰበሩን ተናግረዋል፡፡ በምሥሉ ላይ ተመድ ሰሞኑን  የታደጋቸው ሶሪያውያን ይታያሉ፡፡
source:

No comments:

Post a Comment