Wednesday, February 19, 2014

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ

ኢትዮጵያ ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ
ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የተፈጠረው ቃርኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩት ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒትው ሊቀመንበር እና በመሃበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፌታችን አርብ ፊብርዋሪ 21 / 2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል።
በቅርቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የጠራውን የአባላት ሰብሰባ ተከትሎ የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቀርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ደጋፊዎቻቸውን ወደ አዳራሹ በማስገባት ከማህበሩ ሊቀመንበርነቴ የተነሳሁት ያለአጋባብ ነው በሚል በኮሚኒቲው ሊቀመንበር ላይ ቡጢ በመሰንዘራቸው ተከትሎ በተቀሰቀሰው መለስተኛ ግጨት ስበባው ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሺክ ሙስጠፋ ሁሴን የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21-2014 የኮሚኒቲው ስራ አመራር በጠራው ጠቅላላ የአባላት ጉባኤ ላይ ሁከት ለመፍጠር በብሄር ላይ የተመሰረተ ቀስቀሳዎችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች ከሪያድ አረጋግጠዋል።
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ፊብርዋሪ 14-2014 ምሸት አያሌ ደጋፊዎቻቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኝ አንድ ቢሮ ውስጥ በማን አለብኝነት ሰብሰብው ሲመክሩ መታየታቸውን የሚገልጹት ምንጮች ሼኩ ለግብረ አበሮቻቸው “አማራ ስልጣናችን ስለነጠቀን ማንነታችንን ለማስከበር እና ስልጣናችንን ለማስመለስ እኛ ኦሮምዎች እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ አይገባንም” ብለው በመናገር የጥቂት መስል ደጋፊዎቻቸውን በተሳሳተ መንገድ ቀልብ በመሳብ የኮሚኒቲውን አባላት በዘር በሃይማኖት ከፋፍሎ ለማጋጨት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አጋልጠዋል። የሼክ ሙስጠፋን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ብሄርተኝነትን በስፋት በማራገብ ላይ የተሰማሩት ቅጥረኞች በህገ ወጥ የሃዋላ ንግድ ላይ የተሰማሩ እና ቀደም ሲል በእህቶቻችን ህይወት ዶላር ሲሰብሰቡ የከረሙ የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ኤንጀንሲ ባለቤቶች እና ደላላዎቻቸው መሆናቸውን የሚናገሩ ወገኖች ግለሰቦቹ የትኛውንም በሄር አሊያም የሃይማኖት ተቋም እንደማይወክሉ ገለጸው ህብረትሰቡ ከእንደነዚህ አይነት ሴጣናዊ መርህ ካነገቡ መሰሪዎች እራሱን በመከላከል በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል እንደወትሮው ሁሉ በአንድነት የኮሚኒቲውን ንብረት ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባው መክረዋል።

የቀድሞው የኮሚኒቲ ለቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን በስማቸው በከፈቱት ሁለት ሰራተኛ እና አስሪ አገናኝ እጄንሲ ያስመጦቸው እህቶቻችን በህክምና እጦት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን የሚያስታውሱ ታዛቢዎች ሼኩ በሳውዲ አረቢያ የደህነት ሃይሎች ለእስር በመዳረጋቸውን ተከትሎ በኮሚኒቲው መተዳዳሪያ ህገ ደንብ መስረት የሊቀምንበሩን ቦታ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት ምክትል ሊቀምንበሩ አቶ ቃሲም ያሲን ተረክበው መሸፈናቸው ሊያስመስግናቸው እንጂ ቡጢ ሊያሰነዘርባቸው እንደማይገባ የሚናገሩ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሼኩ ከወህኒ ከወጡ በሃላ ጤንነት እደማይሰማቸው በመጥቀስ የኮሚኒቲ ሊቀምንበርነቴን ለምን በአማራ ብሄር ተነጠኩ በሚል ዘረኝነት የተጠቀሱትን ደጋፊዎቻቸውን በመስብሰብ በአባላቱ መሃከል የብሄር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመጫር እያሰሙ ያለው ጩሀት አብነት መሆኑንን ይገልጻሉ ።
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር በስሩ ከሁለት ሺህ በላይ ህጻናትን ተቀብሎ የሚያስተናገድ አንድ አለም አቀፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባለቤት እንደነበር የሚገልጹ አንጋፋ የማህበሩ አባላት ት/ቤቱን ከኮሚቲው በመነጠል ኤንባሲው በራሱ ስልጣን ባስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ት/ቤቱን እንዳሻው እይዘወረ ላለፉት 4 አመታት ገቢ እና ወጪው ሳይለይ እስካሁንም የጥቂቶች ኪስ ማደለቢያ ሆኖ መቀረቱን ይናገራሉ። ዛሬ በኮሚኒቲው ስራ አመራር እና በሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች መሃከል የተነሳው የስልጣን ሹክቻ ከጥቅም ጋር የተቆራኘ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች በአሁኑ ግዜ ብቸኛ የማህበሩ ንበት የሆነው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል ከት/ቤቱ ባላነሰ ሁኔታ ዘረፋ እየተፈጸመበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፤
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ከ 8 መቶ የሚበልጡ አባላት እንዳሉት የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ማህበሩ የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21 2014 ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ መወሰኑን በመግለጽ በወቅቱ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ኤንባሲው እና የሚመለከታቸው አካላቶች የዜጎቻችን ህይወት ለመታደግ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባቸው አክለው ጠቁመዋል።
ማሳሰቢያ ከዚህ በታች የተመለክተው የቪድዮ ሰዕላዊ መግለጫ ቀደም ብሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ውስጥ ጥቂቶች ብዙሃኑን በዘር በሃይማኖት ሲከፋፍሉት የሚያሳይ ነው።
Ze-Habesha

No comments:

Post a Comment