«የሱዳን መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አከባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሳምንት ዉስጥ ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ መስጠቱ የሑመራና አከባቢው ኗሪዎች ለዓረና ትግራይ ፅሕፈትቤት አስታውቀዋል። የሱዳን መንግስት ትእዛዝ ያስተላለፈው መሬቱ የሱዳን ግዛት ሆኗል በሚል በምክንያት እንደሆነ አክለዋል።” ሲሉ ነበር አቶ አብርሃ የሱዳኖችን እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ ገጻቸው ይፋ ያደርጉት።
በቅርቡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ለሱዳን የተሰጠ ምን መሬት እንደሌል በይፋ መናገራቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ባሉ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ፣ ሱዳኖች ይህን አይነት ከመኖሪያ ቤታችሁ በሳምንት ዉስት ልቀቁ የሚል ማስጠንቀቂያ በሁመራ አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች መስጠታቸው ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጀርባ ፣ እርሳቸው የማያወቁት፣ በሌሎች የአገዛዙ ባለስልጣናት፣ የተወሰኑ ዉሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችል የሚያመላክት ሊሆን እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ።
ሁመራ ኢሕአደግ ስልጣን ከመያዙ በፊት የጎንደር ክፍለ አገር አካል የነበረች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ዉስጥ የተቀላቀለች ቦታ ናት። በሁመራ እንዲሁም ወልቃት ጠገዴ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በቤታቸው አማራኛ ፣ በዉጭ በገበያ ደግሞ ትግሪኛ የሚናገሩ፣ ሁለቱንም ቋንቋዎች በተቀላጠፈ መልኩ የሚያወቁ እንደሆነ ይነገራል። ስለሁመራና ወልቃት ጠገዴ ሲነሳ፣ ምን ያህል «ትግሬ»፣ «አማራ» የሚባለው የዘር ፖለቲካ እንደማይሰራና ብሄረሰቦች በብዙ ቦታዎች እርስ በርስ የተደባለቁና የተዛመዱ መሆናቸውን የሚይሳይ ነዉ።
Source: Abugida
No comments:
Post a Comment