Thursday, February 13, 2014

ሰበር ዜና የደቡብ ሱዳን ጉዳይ እየጋለ ነው።ሻብያ እና ኢህአዲግ/ወያኔ ከሱማልያ ቀጥሎ ለሁለተኛ ጊዜ ደቡብ ሱዳን ላይ በእጅ አዙር ፍልምያ እንዳይገናኙ ያሰጋል።((የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)

ዩጋንዳ ሰራዊቷን በደቡብ ሱዳን ማስገባቷ ኢህአዲግን አላስደሰተም።ባለፈው ሰሞን የደቡብ ሱዳን የዜና ወኪል ይህንኑ ገልጦ ነበር።በሳልቫኪር የሚመራው የደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ መንግስት የዩጋንዳ ጦር መኖሩን የፈለገ መስሏል።በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቸር የሚመሩት የዩጋንዳ ተቃዋሚዎች በሌላ በኩል ”ኢትዮጵያ ጣልቃ ትግባ” ቀረሽ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሬንፊልድ
‘ጉዳያችን ጡመራ’ የደቡብ ሱዳን ጦርነት ሲጀመር ለዩጋንዳው ሙሰቨኒ ጉዳዩ ‘የሰርግ እና ምላሽ ‘ያክል ነው ቀድመው ጦር ሊልኩ የሚችሉ መሪ እንደሚሆኑ ገምታ ነበር።እንዲህ ይነበባል -
አሜሪካ ለጊዜው ጉዳዩ ላይ በቀጥታ መግባት ባትችልም የአካባቢው ሃገራትን ” ‘ቀኝ እጄን ሰጥቻለሁ’ እንደእኔ ሆነህ ይህንን አድርግ” የምትለው ሀገር የሚታዩዋት ምናልባት ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ ብቻ ናቸው።ኢትዮጵያ ደግሞ በአሜሪካ ፍቃድ ብቻ ላለመሄድ የሚያደርጋት የሱዳን ፊት አለ።ሱዳን ተፅኖ ለመፍጠር በኤርትራ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን መሸጋገርያ እንዳትሰጥ ያሰጋል።በመሆኑም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እንደ ሱማሌው ችግር ሙሉ በሙሉ የመግባቷ አዝማምያ እምብዛም አይታይም።ለዑጋንዳው ዩዌሪ ሙሰቨኒ ግን ሰርግ እና ምላሻቸው ነው።” ሰበር ዜና-በደቡብ ሱዳን የሪክ ማቸር ኃይሎች ውግያ ጀመሩ። ትናንት ምሽት ቁልፏን ከተማ ቦርን ተቆጣጠሩ።ኢትዮጵያና ዑጋንዳ በደቡብ ሱዳን አንፃር (ጉዳያችን አጭር ዘገባ ታህሳስ 10/2006 ዓም)ጉዳያችን ታህሳስ 10/2006 ዓም
የአሁኑ ሁኔታ ደግሞ አሜሪካ በሻብያ እና ህወሓት ላይ የተለየ አዲስ ፖሊሲ ልትከተል እንደምትችል ወይንም እንደምትገደድ እንጠብቅ? ጉዳዩን ከሰሞኑ የምናየው ይሆናል።
ጉዳያችን
Source: gudayachn

No comments:

Post a Comment