Monday, February 10, 2014

አቶ አስራት ጣሴ ወደ እስር ሲወሰዱ የሚያሳይ ቪዲዮ


ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡
አቶ አስራት ጣሴ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ3 ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ምክን ያቱ ለጊዜው ግልፅ ባልሆነ ውሳኔ ወደ ቂሊንጦ ከፍተኛ ጥበቃ ወህኒቤት እንዲዛወሩ መደረጉን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡

የፖሊስ ምንጮቹ እንዳሉት ኦአስራት በፖሊስ ጣቢያው በቆዩባቸው ጊዜያት በእስረኛው ተገቢው አክብሮትና መልካም አቀባበል ማግኘታቸው አሳሪዎቻቸውን አላስደሰተም፡፡

አንድነት ፓርቲን ከምስረታው ጀምሮ በከፍተኛ አመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በአሁኑ ወቅትም በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤትና ስራ አስፈፃሚ የፓርቲዎችን ውህደት እንዲመሩና የአማካሪ ምክርቤት እንዲያቋቁሙ ኃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ አንድነት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትህ” በሚል መሪቃል የመንግስት የተለያጡ ሀላፊዎችን ለመክሰስ እንቅስቃሴ ማድረጉን ተከትሎ መንግስትም የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን ምክንያት እየፈለገ መክሰስና ማሰር መጀመሩ ገዢው ፓርቲ አለመረጋጋት ውስጥ እንደገባ የሚያመላክት ነው፡፡

ዳንኤል ተፈራ ቃል እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ
የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡ ፍኖተ ነፃነት ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧይታወሳል፡፡

via: Minilik Salsawi

No comments:

Post a Comment