Thursday, February 6, 2014

ከማዕከላዊ እስር ቤት 4 ሙስሊሞች መፈታታቸው ተገለፀ፡፡

ከአራት ወራት በላይ በማዕከላዊ እስር ቤት ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ሲፈፀመባቸው ከቆዩ ሙስሊሞች መካከል 4 የሚሆኑት ሙስሊሞች ከእስር መለቀቃቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

አራቱ ሙስሊሞች ወረቀት በመበተን በሚል ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት በቀነ ቀጠሮ ሲጉላሉ ከቆዩ ቡሃላ ዛሬ ከሰአት በፊት ከእስር ቤቱ ውጡ ተብለው እንደተለቀቁ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከማዕከላዊ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ሲፈፀመባቸው ከመቆቱም በተጨማሪ ቤተሰብም እንዳይዘይራቸው ለበርካታ ጊዜ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ከማዕከላዊ ማሰቃያ ቤት የተለቀቁት 4ቱ ሙስሊሞች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

1. መስፍን ገብሬ ወይም ሃቢብ
2. አብዱላሂ ከሊል
3. ኡመር ሽኩረላህ
4. ሙጂብ አሚኖ ናቸው፡፡

Via:Minilik Salsawi

No comments:

Post a Comment