Tuesday, January 7, 2014

ሕዝባዊ ብሶት – የከተማ አብዮት? – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ባለፈው ሳምንት ኢህአዴግ በከተሞች ላይ የቋጠረውን ስር የሰደደ ጥላቻ ከነመግፍኤው ጨርፈን ከተመለክተን በኋላ፤ ለዛሬ፣ ታላላቅ ግድፈቶቹ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅኦና በአደባባዩ የሚነሱትን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመዘርዘር፤ እንዲሁም ‹‹ማኦኢዝም›› የሚበይነውን ከገጠር የሚነሳ ብረታዊ ትግል፣ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት አንፃር ለመፈተሽ ቀጠሮ መያዛችን ይታወሳል፡፡ እናም እንዲህ እንቀጥላለን…

የኢህአዴግ ግድፈቶች:- ፈረንጅኛው ‘Achilles Heels’ በሚል ስያሜ የሚገልፃቸው እና አማርኛው ደካማ ጎኖች ብሎ የሚሰይማቸው የስርዓቱ ታላላቅ ግድፈቶች ከዕለት ዕለት ራሳቸውን ማብዛታቸው ፍፃሜው የሚተነበይ አድርገውታል፤ ይኸውም ብሔር ተኮር ጥያቄዎች አለመመለሳቸው፣ ውጤት አልባው የገጠር ፖሊሲ፣ የድህረ-ደርግ የዴሞክራሲ ሽግግሩ መክሸፍ (ከፖለቲካ፣ ከሰብዓዊ እና ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንፃር)፣ የኢኮኖሚ እድገት አለመኖር፣ ድህነት ከቀድሞውም በበረታ መልኩ መስፋፋቱ፣ የትምህርት ፖሊሲው ክስረት፣ የስራ-አጥ ቁጥር አለቅጥ ማሻቀብ፣ የራስ አስተዳደር (Self-adminstration) ሙሉ ለሙሉ አለመተግበር (ከስልጤ እስከ ቁጫ ያሉ የማንነት ጥያቄዎች መቆሚያ ማጣታቸው)፣ የመሬት ፖሊሲው የአርሶ አደሩን የነፍስ ወከፍ የይዘት መጠን ከአንድ ሄክታር ማሳነሱ፣ የከተሞች ስራ-አጥነት በወጣት ከተሜ የተማሩ ልጆች ላይ መብዛቱ፣ በልማታዊ መንግስት ትግበራ እና በብሄር ፌደራሊዝም መሀከል የማይታረቁ ቅራኔዎች መኖራቸው፣ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲመጣ በብሔር ፖለቲካ ሞት ላይ ግለሰባዊነት እንደሚነግስና ኢህአዴግም ይህንን ተቃርኖ ተከትሎ የርዕዮተ-ዓለም መሸጋሸግ ማድረግ የማይችል መሆኑ እና መሰል ተቋማዊ ክስረቶች በቀጣይ ሊያርማቸው የማይቻለው ታላላቅ ግድፈቶች በመሆናቸው እንደተለመደው …
... click here to continue reading

No comments:

Post a Comment