Friday, November 14, 2014

ቃለ ምልልስ…. በሊባኖስ ከ4ኛ ፎቅ ከወደቀችው ከእህት ብርቱካን ጋር


ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ
አንዲት እህት ከአራተኛ ፎቅ የመውደቋ መረጃ በሊባኖስ መገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ ከነሰቅጣጭ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ነበር ፣ ኢትዮጵያዊቷ እህት ብርቱካን ነበረች ! ለኦማን የአካል ጉዳተኛ ሆና ሃገር ቤት የገባችው በአልማዝ ጉዳት ስንቆሰዝምና ” የረጅ የደጋፊ ያለህ !” በማለት እርዳታ ስናሰባስን ከወደ ሊባኖስ ቤሩት በእህት ብርቱካን ላይ ሆኖ አይተነው የሰቀጠጠን ፣ ሰምተነው ያመመን አደጋ ልባችን ሰበረው: (
birtukan
ብዙም ሳይቆይ በብርቱካን ዙሪያ አወዛጋቢ ሪፖርቶች መቅረብ ጀመሩ ፣ እድሜ ለሥነ ቴክኖሎጅ ወሎ አድሮ ነገሩ እየጠራ መጣ ! በሊባኖስ ከሚገኙ ለሰብዕና ባደሩ ቅን ወዳጆቸ ትብበር የብርቱካንን ጉዳይ በቅረብ በመከታየል ብርቱካን ያለችበት ሁኔታ በአንደበቷ እንድታስረዳን ያደረግነው ጥረት ተሳክቷል ! ከብርቱካን በተጨማሪ ጉዳዩ ሚመለከታቸውን ሃላፊዎችና ሃኪሞች በጉዳቷ ዙሪያ አነጋግሬያቸውም ነበር ። የህክምና ባለሙያዎችና በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ሃላፊዎች እንዳሉት ከሆነ ብርቱካን የደረሰባት ጉዳት ለከፋ አደጋ ስላልዳረጋት በቀጣይ ቀናት ከሀኪም ቤት በመውጣትና በተዘጋጀላት ማረፊያ ሆና ህክምናና ጉዳይዋን በፍርድ ቤት እንደምትከታተል ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ያስረዳሉ ።
ከዚህ በማስከተል በትናንት ሃሙስ ህዳር 3 ቀን 2007 ከቀትር በኋላና አመበሻሹ ላይ እኔ ከሳወዲ ጅዳ ብርቱካንን ከሊባኖስ ቤሩት ሆስፒታል በመሆን በስልክ ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ትከታተሉት ዘንድ ግብዣየ ነው !
ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 4 ቀን 2007 ዓም
-- Ze-Habesha Website 

No comments:

Post a Comment