Wednesday, September 24, 2014

ፌስቡክ ወርሃዊ ክፍያ ሊጠይቅ ነው

ከ1 ነጥብ 317 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስቡክ የተሰኘው ማህበራዊ ድረገፅ ከህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ተጠቃሚዎች በየወሩ ሶስት የአሜሪካን ዶላር (60 ብር ገደማ) እንዲከፍሉ ወሰነ።
facebook-addiction
የፌስቡክ መሥራችና ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ማርክ ዙክምበርክ ከትላንት በስቲያ በአሜሪካን ሀገር በጉዳዩ ላይ ይፋዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ለወርሃዊ ክፍያው የሰጡት ምክንያት የአስተዳደራዊ ወጪ እየናረ መምጣትን ነው።
ፌስቡክ አሁን ካሉት 1 ነጥብ 317 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች 75 በመቶ ያህሉ በየወሩ የአባልነት 3 ዶላር ሊሰበስብ እንደሚችል የገመተ ሲሆን ይህም ገንዘብ በዓመት እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኝለታል።
የፌስቡክ ቃለአቀባይ ሚስተር ፓውል ሆናነር ስለጉዳዩ ለሲ.ኤን. ኤን የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት አስተያየት በየቀኑ ፌስቡክን በ100ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚቀላቀሉ አስታውሰው የወርሃዊ የአባልነት ክፍያው መጣሉ ፌስቡክም ራሱ እንዳላስደሰተው ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የፌስቡክ አካውንት ያላቸው ከ902 ሺ 440 በላይ ያህል ዜጎች መሆናቸውን መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን በሀገሪቱ ካለው የውጪ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ ዶላር በባንክ ማስተላለፍ ስለማይቻል በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የማኅበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ከአገልግሎቱ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ የብዙዎች ግምት ሆኗል።

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

No comments:

Post a Comment